ባንካችን መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የ4 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ

ባንካችን መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የ4 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ አደረገ

ባንካችን አቢሲንያ መጪውን የዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ ዛሬ  ዿግሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖቻችን 4 ሚልዮን ብር የሚወጣ የአስቤዛ ድጋፍ አደረገ።  

ማህበራዊ ሃላፊነትን መወጣት ዋነኛ መገለጫው እና ቁልፍ ተቋማዊ ዕሴቱ የሆነው ባንካችን አቢሲንያ ይህን የአይነት ድጋፍ ያደረገው በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ አረጋውያን፣ወላጆቻቸውን ላጡ ሕጻናትና ሴቶች ነው።

የባንካችን ቺፍ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ አብርሃም ገበየሁ እና ሌሎች የባንካችን የስራ ሃላፊዎች ድጋፉን ለገሀር በሚገኘው በትንሿ ስታዲየም ተገኝተው አስረክበዋል።

አቶ አብርሃም ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ “ድጋፉ በመጪው የዘመን መለወጫ በዓል ባንካችን አቢሲንያ ከጎናችሁ እንደሆነና አጋርነቱን ለማሳየት ያደረገው ተግባር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።   

በዝግጅቱ ላይ የለሚኩራ፣ የልደታ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 7 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ነኢማ ሎባ በበኩላቸው ባንካችን በየጊዜው ለተቸገሩ ወገኖቻችን የሚያደርገውን ድጋፍ በማድነቅ በወረዳቸው ስም አመስግነዋል፡፡

ድጋፉ በነገው ዕለትም በከተማችን አዲስ አበባና በቢሾፍቱ ለሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖቻችንም የሚደረግ ይሆናል፡፡

Call Now Button