ትናንት ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው የባንካችን አቢሲንያ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የባንካችን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለተሰብሳቢው አቅርበው ውይይት ሲደረግባቸው ውሏል።
በጉባዔ የትናንት የጠዋት ውሎ በቅድሚያ የባንካችን የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኤልሳቤት ገብሩ ተሰብሳቢውን “እንኳን ደህና መጣችሁ ! ” ካሉ በኋላ የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉና ጉባዔውን በይፋ እንዲያስጀምሩ ጋብዘዋል።
የአቶ በቃሉን የመክፈቻ ንግግር ተከትሎም የባንካችን የስትራቴጂና ሪሰርች መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ታምራት የ2025/26 በጀት ዓመት ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው በተሰብሳቢዎቹ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በጉባዔው የከሰዓት ውሎ ደግሞ የባንካችን አስሩም ዲስትሪክቶች እንዲሁም የተለያዩ የዋናው መ/ቤት የሥራ ክፍሎች የሥራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበው በተሰብሳቢው ጥልቅ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በዚህ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣የባንካችን ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ የዲፓርትመንት ዳይሬክተሮች፣ የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች፣ በአ.አ የሚገኙ ቅርንጫፍ ስ/አስኪያጆች እና የዲቪዥን ስ/አስኪያጆች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ጉባዔው ዛሬም ቀጥሎ የሚውል ይሆናል።




















