ባንካችን አቢሲንያ በ2025/26 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሶስት ዲስትሪክቶች የዕውቅና ሽልማት አበረከተ።
ሽልማቱ የተበረከተው ትናንት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሸራተን አዲስ በድምቀት በተከናወነው የባንካችን ዓመታዊ የስኬት እና ልምድ ልውውጥ (Dine and Learn with the CEO) መድረክ ላይ ነው።
በዚህም መሠረት በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡት ለባህርዳር፣ ምስራቅ አዲስ እና መካከለኛው አዲስ ዲስትሪክቶች የባንካችን ዋና ስ/አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ የዋንጫ እና የሰርተፍኬት ሽልማት አበርክተዋል።
እንዲሁም በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ (Deposit mobilization ) የላቀ ስኬት ላስመዘገበው የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷል።
ከዚህም በተጨማሪ በአፈጻጸማቸው የተሻለ ውጤት ላመጡ 30 የቅርንጫፍ ስ/አስኪያጆች እና ከላይ ከጠቀስናቸው ሶስት ዲስትሪክቶች ለተመረጡ 12 ሠራተኞች በጠቅላላው ለ 42 ሠራተኞች ባንካችን የአጭር ቀናት የውጭ ሃገር የስልጠና ዕድል አመቻችቷል።








