ባንካችን አቢሲንያ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2018ዓ.ም ከጫካ ቡና ጋር በመተባበር ለገሃር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓልን በደማቅ ዝግጅት አከበረ፡፡
በዚህ ዝግጅት ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ ወጣት ወንዶች በባሕላዊ አልባሳት አሸብርቀው የ‹‹ሆያ ሆዬ›› ባሕላዊ ጭፈራን ደማቅ በሆነ ሁኔታ ተጫውተዋል፡፡
ወጣቶቹ በባንካችን ሒሳብ የከፈቱ ሲሆን፣ ባንካችንም የመጀመሪያውን ተቀማጭ ገንዘብ በስጦታ መልክ አበርክቶላቸዋል፡፡
በዚህ መሰናዶ ላይ የባንካችን የሥራ ኃላፊዎች እና የጫካ ቡና ባለቤትና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
ባንካችን ከዚህ ቀደምም ኃይማኖታዊና ባሕላዊ ይዘት ያላቸውን መሰል ክንውኖች ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፉ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ የቆየ ሲሆን፣ ወደፊትም ይህንኑ ተግባሩን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡








