ባንካችን አቢሲንያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
ይህን ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሠቢያ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረምየኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በንግግር ከፍተውታል።
ይህ የፋይናንስ ተቋማት፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ የግል ተቋማት ተወካዮች … ወዘተ የሚገኙበት ፎረም በዋነኝነት እነዚህ ተቋማት ልምድ የሚለዋወጡበት እና በሃገራችን የወደፊት የፋይናንስ ሁኔታ ላይ የሚመክሩበት መድረክ ነው።
ባንኮች እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት ኤግዚቢሽንም ሌላው የዚህ ፎረም አካል ሲሆን፣ ባንካችንም በተወካዮቹ በኩል በተለይም የወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎቱን እና ሌሎች የዲጂታል አገልግሎቶቹን ለፎረሙ ተሳታፊዎችና ጎብኚዎች በስፋት እያስተዋወቀ ይገኛል።
በቀጣዮቹ ሦስት ቀናት በሚቆየው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝን ጨምሮ፣ የፋይናንስ እና የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።





