ባንካችን በ7ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የህብረተሰብ ንቅናቄ ላይ ተሳተፈ

ባንካችን በ7ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የህብረተሰብ ንቅናቄ ላይ ተሳተፈ

ባንካችን አቢሲንያ “ንቁ ዜጋ ደህንነቷ ለተጠበቀ ሃገር” በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ – ኢንሳ) አስተባባሪነት በተዘጋጀው እና ከጥቅምት 1 ጀምሮ አየተከበረ በሚገኘው 7ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ላይ ተሳተፈ።

ወሩ የተቋማትን እና የህብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ለማጎልበት፣ በተለይም ደግሞ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትግበራን የሚደግፉ ንቅናቄዎችን ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው፡፡

ባንካችን አቢሲንያም የዚህን ንቅናቄ የጎላ ጠቀሜታ በመረዳት ለዝግጅቱ መሳካት የብር 5 ሚሊዮን የወርቅ ደረጃ የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ አበርክቷል።

ባንካችን ይህን በማድረጉ የደንበኞቹን ደህንነት በማረጋገጥ ዕምነታቸውን ከፍ ከማድረጉም በተጨማሪ፣ ፕሮዳክቶቹን እና አገልግሎቶቹን ለህብረተሰቡ የበለጠ አስተዋውቋል።

የተለያዩ ጉባዔዎች፣ የሳይበር ደህንነት ታላቁ ሩጫ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች … እንዲሁም ሌሎች ሁነቶች ለአንድ ወር የሚቆየው የዚህ ሃገር አቀፍ ንቅናቄ አካል ናቸው

Call Now Button