ባንካችን ለቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት የብር 300,000 ተጨማሪ ድጋፍ አደረገ

ባንካችን ለቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት የብር 300,000 ተጨማሪ ድጋፍ አደረገ

ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና የማኅበረሰባችንን ችግሮች ለማቃለል ሁሌም የሚተጋው ባንካችን አቢሲንያ ለቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት የብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

እንደሚታወሰው በዚህ ድርጅት ስር የሚረዱ ሕፃናት እና ታዳጊዎች በባንካችን ዋና መ/ቤት በመገኘት የ2019 አዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የ“አበባ አየሽ ሆይ” ዜማን በተጫወቱበት ወቅት ባንካችን የብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የገንዘብ ስጦታ አበርክቶ ነበር። 

በወቅቱ በተቋሙ በጎ ተግባራት የተደነቁት የባንካችን የሥራ ኃላፊዎች ድርጅቱን ለመጎብኘት ቃል በገቡት መሠረት ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም በተቋሙ ቅጥር ጊቢ ተገኝተው ጉብኝት አከናውነዋል ተጨማሪ ድጋፉም አበርክተዋል፡፡

የባንካችን ቺፍ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ አብርሃም ገበየሁ የገንዘብ ስጦታውን ካበረከቱ በኋላ፣ ሕፃናት ላይ በመሥራት ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የተናገሩ ሲሆን፣ ይህን ሥራ እየሠራ የሚገኘውን ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅትም አመስግነዋል።

አቶ አብርሃም አክለውም “በጉብኝቱ ወቅት ባየነው ነገር በጣም ተደስተናል፤ ባንካችን አቢሲንያም ከጎናችሁ ነው” ብለዋል፡፡

የቶራ በጎ አድራጎት ድርጅት  ዋና ሥ/አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሳምሶን ገብረ እግዚአብሔርም በበኩላቸው ባንካችን ላደረገላቸው ተጨማሪ የገንዘብ ስጦታ ከልብ አመስግነዋል፡፡

ቶራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከተቋቋመበት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወላጅ አልባ ሕፃናትን እና በችግር ውስጥ ያሉ ሴቶችን በምግብ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እንዲሁም የሙያ ክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት እየደገፈ የሚገኝ ተቋም ነው።

Call Now Button