የተከበራችሁ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ባአክሲዮኖች
በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የተሻሻለው የመመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 20 መሠረት የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 30ኛ መደበኛ እና 17ኛ አስቸኳይ ጉባዔዎች ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ የፓን አፍሪካ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔዎቹ ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
| የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤ/ቁ. 351/1 | የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር KK/AA/2/0001775/2004 የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- በባንክ ሥራ ላይ የተሠማራ |
| የባንኩ ድረ-ገጽ፡- https://www.bankofabyssinia.com | አክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ፡- 17,481,120,000 |
| የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. | አክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ፡- 17,481,120,000 |
1. የ30ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1.1. አጀንዳዎቹን ማጽደቅ፤
1.2.አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደርጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፤
1.3. ጊዜያዊ የቦርድ ዕጩዎች ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ፤
1.4. ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ መቀበል፤
1.5. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፤
1.6. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት ማዳመጥ፤
1.7. በተራ ቁጥር 1.5 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
1.8. በተራ ቁጥር 1.6 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
1.9. እ.ኤ.አ. በ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፤፤
1.10. እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያን መወሰን፤
1.11. እ.ኤ.አ. የ2026/2027 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርኃዊ የአበል ክፍያ መወሰን
1.12. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፤
2. የ17ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1. አጀንዳዎቹን ማጽደቅ፤
2.2. የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በዳይሬክተሮች ቦርድ በሚቀርበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
2.3. የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፤
3. ማሳሰቢያ
3.1. በጉባዔው መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውና ፎቶኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከ3 የሥራ ቀናት በፊት ለገሀር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮንና ኢንቨስትመንት ክፍል ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምፅ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን ባክብሮት እንገልጻለን። ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን፣ እንዲሁም የባንኩ ሠራተኞች ለባለአክሲዮኖች ወኪል በመሆን በጉባዔዎቹ ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
3.2. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ እና የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ዋናውንና ኮፒውን በመያዝ፤እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዛችሁ መቅረብ ያለባችሁ መሆኑን ባክብሮት እናሳውቃለን።
የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave a Reply