5ኛ ዙር እችላለሁ
ማርች 8 ን በማስመልከት የተዘጋጀ የስራ ፈጠራ ሃሳብ እና የፕሮዳክት ማስታወቂያ የቲክቶክ ውድድር መስፈርቶች
ባንካችን አቢሲንያ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ን በማስመልከት ለ5ኛ ጊዜ “እችላለሁ (I CAN)” በሚል መሪ ቃል ልዩና ሴቶችን የሚያበረታታ መርሐ-ግብር ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል።በዚህ ዓመታዊ መርሐ-ግብር ከተካተቱ እና ሽልማት ከሚያስገኙ ውድድሮች መካከል አንዱ ሴት ተወዳዳሪዎች የአደይ እና ዘህራህ የቁጠባ ሒሳቦችን በፈጠራ ሥራ የሚያስተዋውቁበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የሥራ ፈጠራ ሐሳብ ኖሯቸው የገንዘብ እገዛ የሚፈልጉ ሴቶች የተወዳደሩበት መርሐ-ግብር ነበር።
ባንካችን አሸናፊዎቹን ለመለየት የተጠቀመባቸውም መስፈርቶች እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል።
የስራ ፈጠራ ሃሳብ የውድድር መስፈርቶች
የዲጂታል ውጤት(40%):
• የቪዲዮ እይታ
• ኢንጌጅመንት
• የውድድሩን ህጎች መከተል
• የቪድዮው ሃሳብ የተገለጸበት መንገድ
የስራ ፈጠራ ሃሳብ በኮሚቴው የተገመገመ (60%):
• የንግዱ ሃሳብ እና ወደፊት እየሰፋ የሚሄድ መሆኑ
• የገንዘቡ ለንግዱ በቂ መሆን
• የንግድ ሥራው ተግባራዊነት
• የስራ ሃሳቡ ከተለመደው ለየት ማለቱ
የፕሮዳክት ማስታወቂያ(አደይ እና ዘህራህ የቁጠባ ሂሳብ) የውድድር መስፈርቶች
የዲጂታል ውጤት(100%):
• የቪዲዮ እይታ
• ኢንጌጅመንት
• የውድድሩን ህጎች መከተል
• የቪድዮው ሃሳብ የተገለጸበት መንገድ