Blog

የዲጂታል ግብይትና ደንበኞች ሊገነዘቧቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነጥቦች

የዲጂታል ግብይትና ደንበኞች ሊገነዘቧቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነጥቦች

ከቅርብ አመታት ወዲህ በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘው የዲጂታል ግብይት ዘርፍ ብዙዎች በሚፈጽሙት ግዢ፣ ንግድ በሚከወንበት አግባብና በግብይት ወቅት በሚስተዋሉ የግብይት ዝንባሌዎችን በአዲስና ከዚህ ቀደም ባልተስተዋለ መንገድ በመቀየር አዲስ የግብይት ስርዓትን ይዞ ቀርቧል፡፡ በዚህ ረገድም የዲጂታል ግብይት ዘዴዎች በብዙዎች የዕለት ተዕለት የኑሮ ክንውን ውስጥ በዋነኛነት ይዘውት በቀረቡት ምቾት፣ ቅልጥፍናና አማራጭ አንጻር ይህ ነው የማይባል ቦታን መያዝ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአለም ዙሪያ በብዙዎች ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘውን የዲጅታል ግብይትን በቁጥሮች በማስደገፍ ስናስቀምጠው ከጠቅላላው የአለም ህዝብ 33 በመቶ የሚሆነው የዲጅታል ግብይትን የዕለት ተዕለት ህይወቱ አንድ አካል በማድረግ ግብይትን በዚሁ ስርዓት የሚፈጽም ሲሆን ይህም በአመት ከ 6.8 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይገመታል፡፡  የዲጅታል  ግብይት ምንድነው ?          ከርዕሱ ለመረዳት እንደሚችለው የዲጅታል ግብይት አማራጭ በአጭሩና ብዙሀኑን በሚያግባባ ሁኔታ ሲቀመጥ ኢንተርኔትን ማለትም ኤሌክትሮኒክ ዘዴን በመጠቀም ቁሶችን ወይም አገልግሎቶችን ለመግዛት አልያም ለመሸጥ የሚያስችል የግንኙነት ዘዴ ተብሎ ሊወሰድ ይቻላል፡፡ በመሆኑም ይህ የግብይት ዘዴ በምርት እና አገልግሎት አቅራቢ እና በደንበኛው መካከል ድልድይ በመሆን ቀላል እና ቀልጣፋ ግብይት እንዲከወን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ስለ ዲጅታል የግብይት ዘዴዎች ይህን ካልን ምን ዓይነት የዲጅታል ክፍያ ዘዴዎችን በሰፊው በጥቅም ላይ በመዋል ላይ እንደሚገኙ ከዚህ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡  1.   ነጋዴ – ለደንበኛ (B2C): በዚህ የዲጅታል ግብይት ስርዓት የተለያዩ የንግድ ተቋማት ለደንበኞቻቸው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን በቀጥታ ተደራሽ የሚያደርጉበት አሰራር ሲሆን በአለም ዙሪያ እንደ አሊባባና (Alibaba) አማዞን...

Read More
9ኙ ደንበኛ ተኮር ማሻሻያዎች !

9ኙ ደንበኛ ተኮር ማሻሻያዎች !

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ከግንባር ቀደሞቹ ተዋናዮች መካከል አንዱ የሆነው አቢሲንያ ባንክ እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን የዲጂታል ፋይናንስ ፍላጎት ለማርካት በስራ ላይ...

Read More
Call Now Button