አቢሲንያ ባንክ በቅርቡ በተካሄደው 23 ኛው ኮኔክትድ ባንኪንግ ስብሰባ (23rd Edition of Connected Banking Summit – Innovation and Excellence Awards Ethiopia!) ላይ የፈጠራ ልህቀት ተሸላሚ ሆኗል።
ይህንንም የፈጠራ ልህቀት (𝐄𝐱𝐜𝐞𝐥𝐥𝐞𝐧𝐜𝐞 𝐢𝐧 𝐈𝐧𝐧𝐨𝐯𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧) ሽልማት የአክሴፕታንስ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ተዎድሮስ አባይ ነሃሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት ላይ ባንኩን ወክለው ተቀብለዋል።
ይህ ሽልማት ባንካችን የደንበኞች ተሞክሮን (Customer Experience) ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግና አስቀድሞ መፍትሄ ለማበጀት ላደረገው ያላሰለሰ ጥረትና በሃገራችን የባንክ አገልግሎት ላይ ላሳረፈው ጉልህ አሻራ የተሰጠ ዕውቅና ነው።
ባንካችን አቢሲንያ የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶችንና ፕሮዳክቶችን ለደንበኞቹ ከማስተዋወቅ አንስቶ እጅግ በጣም ዘመናዊና ከወቅቱ ጋር የሚሄዱ ቴክኖሎጂዎችን በስራ ላይ በማዋል ረገድ ብዙ ርቀት ተጉዟል።
በቅርቡም ከ920 በላይ በሆኑትና በመላ ሃገሪቱ በሚገኙት ቅርንጫፎቹ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታል፣ ወረቀት አልባና ጥሬ ገንዘብ አልባ (Cashless) አገልግሎትን ስራ ላይ ማዋሉ የሚታወስ ነው።


Leave a Reply