ባንካችን አቢሲንያ በተጠናቀቀው የ2025/26 በጀት ዓመት ከፍተኛ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ ይህም ከዕቅዱም ሆነ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር ትልቅ ብልጫ የታየበት ሆኗል። በበጀት ዓመቱ አስቸጋሪና ፈታኝ የኢኮኖሚና የቢዝነስ ተግዳሮቶች ተከስተው የነበረ ቢሆንም እንኳን፣ ባንካችን ከዕቅዱም ሆነ ካለፈው በጀት ዓመት የተሻለ ተቀማጭ ገንዘብ በመሰብሰበ የአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡን መጠን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የደንበኞችን ፍላጎት...
Category: News
ባንካችን የደንበኞች የዕውቅና እና የምስጋና ቀንን በደማቅ ዝግጅት አከበረ
ባንካችን አቢሲንያ ትናንት ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የደንበኞች የዕውቅና እና የምስጋና ቀንን ምክንያት በማድረግ ረጅም ጊዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞቹን እና አጋሮቹን በመሸለም እና ዕውቅና በመስጠት በሸራተን አዲስ በደማቅ ዝግጅት አከበረ። በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ “የዝግጅቱ ዓላማ ባንካችን ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር፣ ለአስተዋፅኦዋቸው ምስጋና ማቅረብና...
ባንካችን የዓለም ዋንጫን አስመልክቶ ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ዕድለኛውን ሸለመ
ባንካችን በሁለተኛው ዙር 2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን አስመልክቶ ባዘጋጀው የሽልማት መርሀ ግብር የላፕቶፕ ዕድለኛ ለሆኑት ደንበኛ ትናንት ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ሽልማታቸውን አስረክቧል። ባንካችን ከቪዛ ጋር በመተባበር በመጀመሪያው ዙር ደንበኞች የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን ተጠቅመው ግብይት ሲፈጽሙ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በቀጥታ የመመልከት ዕድል የሚያስገኝላቸውን ታላቅ የሽልማት ፕሮግራም አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፣ ዕድለኛ ደንበኞችም ጨዋታውን እየታደሙ...
ባንካችን የ2026 ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ ለወጣላቸዉ ዕድለኞች የሽኝት መርሐ-ግብር አካሄደ
ባንካችን “አቢሲንያ- ቪዛ 2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ” በሚል መጠሪያ ከቪዛ ጋር በጋራ ባካሄደው የሽያጭ ዘመቻ ላይ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ ለወጣላቸዉ አራት ዕድለኞች የሽኝት መርሐ-ግብር አካሄደ። ትናንት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በባንካችን ዋና መ/ቤት በተካሄደው የሽኝት መርሐ-ግብር ላይ የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ እንደተናገሩት እነዚህ ዕድለኞች አስፈላጊውን የጉዞ ፈቃድ ያገኙና የ2026...
ባንካችን ቃል በገባው መሠረት 2 ዘመናዊ መኪኖችን ለዕድለኞች አስረከበ
ባንካችን አቢሲንያ በቅርቡ ባካሄዳቸው ሁለት የሽያጭ ዘመቻዎች የዘመናዊ መኪና ሽልማት አሸናፊ ለነበሩ ሁለት ደንበኞች ዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት በተካሄደ ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ሽልማታቸውን አስረከበ። በዚህም መሠረት ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ”የሽልማት መርሐ-ግብር አሸናፊ ለሆኑት የባንካችን የፍልውሃ ቅርንጫፍ ደንበኛና በከተማችን በአንድ የግል የህክምና ክሊኒክ ሐኪም ለሆኑት ዶ/ር...
የባንካችን የ2ኛ ዙር የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ሽልማት የመጀመሪያዎቹ 2 ዕድለኞች ሽልማታቸውን ተቀበሉ
ደንበኞች የዲጂታል አማራጮችን በስፋት እንዲጠቀሙ የሚያበረታታው የባንካችን የ2ኛ ዙር የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ የሽልማት ፕሮግራም የመጀመሪያ ሁለት ዕድለኞች ሽልማታቸውን ተቀበሉ። ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት አዳራሽ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ላይ ይፋ እንደተደረገው የባንካችን የአፖሎ ዲጂታል ባንክ ደንበኛ የዘመናዊ ስልክ ሽልማት ሲቀበሉ የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት፣ ኮተቤ ወልገሞ ቅርንጫፍ ደንበኛ ደግሞ የ10,000 ብር የፕሪፔይድ ካርድ ሽልማት...
ባንካችን አቢሲንያ ከደቡብ አፍሪካው አብሳ ባንክ ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ
ባንካችን አቢሲንያ ከደቡብ አፍሪካው አብሳ ባንክ (Absa Corporate and Investment Bank) ጋር ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የልምድ ልውውጥ አካሄደ። በዚህ እርስ በርስ የመማማር እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ የአብሳ ባንክ የአመራር ብቃት ማሳደጊያ መርሐ ግብር (Absa Development Initiative – ADI) አካል የሆኑ 30 ከፍተኛ ሥራ አስኪያጆች እና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል። በመድረኩ...
ባንካችን የ“እችላለሁ!” የሽልማት መርሐ-ግብር የቤት መኪና ዕድለኛን ይፋ አደረገ
ባንካችን አቢሲንያ ማርች 8 ን በማስመልከት ለ5ኛ ጊዜ ያከናወነውን የ“እችላለሁ (I CAN)” መርሐ-ግብር በማጠናቀቅ የ2025 ቢ.ዋይ.ዲ ሴጉል ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አዳራሽ አከናውኗል። ይህን የባንካችን የሥራ ሐላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙበትን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት የባንካችን ቺፍ ኤንተርፕራይዝ ሰርቪስ ኦፊሰር...
ለባንካችን ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ
ለአቢሲንያ ባንክ ከፍተኛ አመራሮች ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም “የከፍተኛ አመራሩ አርዓያነት ለፀረ-ሙስና ትግሉ ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ ቃል በስካይ ላይት ሆቴል ስልጠና ተሰጠ።ይህን “በስነ- ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስልጠና የባንኩ ዋና የኮርፖሬት የሰው ሃብት አስተዳደር ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰይፉ ቦጋለ በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ባንኩ የራሱ የሆነ ጠንካራ...
ባንካችን አቢሲንያ “ከክፍሏ አትቅር!” በሚል መሪ ቃል ለሴት ተማሪዎች የ 1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
ባንካችን አቢሲንያ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ በሚገኘው አቢሲንያ አሚን በኩል፤ የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ጉዞ ለማቃናት ያለመ የድጋፍ መርሐ ግብር አከናወነ።ባንኩ ተፈጥሯዊ ዑደትን ተከትሎ የሚመጣውን የትምህርት መስተጓጎል ለመቅረፍ ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 በሶስት የትምህርት ተቋማት በመገኘትና ከሐንስ ውመን ኬር ጋር በመተባበር ባደረገው የ 1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የንፅህና መጠበቂያ...









