bankofabyssinia.com

ባንካችን አቢሲንያ በሐምሌ ወር የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 94 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አቀረበ!

ባንካችን አቢሲንያ በሐምሌ ወር የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 94 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አቀረበ!

አቢሲንያ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታት ብሎም በኢኮኖሚው የዋጋ መረጋጋት አንዲኖርና የደንበኞችን የገቢ ንግድ ለመደገፍ የበኩሉን አስተዋፆ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ በተለይም ለምግብ፣ እንዲሁም ለሌሎች ወደ ሀገራችን ለሚገቡ ስልታዊ ሸቀጦች (Strategic Commodities) ቅድሚያ በመስጠት ለደንበኞቹ በተለያየ መጠን የውጭ ምንዛሬ ሲያቀርብ ቆይቷል።
በሐምሌ ወርም ባንካችን ከደንበኞቹ ለቀረቡት በርካታ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ጥያቄዎቹን ያስተናገደ ሲሆን፣ በድምሩ ወደ 94 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በተለያየ ዘርፍ ለሚሠሩ ደንበኞች አቅርቧል።
በዚህ ወር ከቀረበው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ 32 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለምግብ እንዲሁም ወደ 62 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለሌሎች ወደ ሀገራችን ለሚገቡ ስልታዊ ሸቀጦች ድልድል አድርጓል። አሁን ላይም ባንካችን የደንበኞቹን የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ለማርካት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ሲሆን በቀጣይም በደንበኞች የሚቀርቡ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄዎችን ለመመለስ በተመሳሳይ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በአክብሮት ይገልጻል።
አቢሲንያ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ሀብቱን በአግባቡ በማስተዳደር፣ ከአገራዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር በማጣጣም ግልጽና ፍትሀዊ የውጭ ምንዛሪ ድልድል ተግባራዊ በማድረግ፣ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን የሚቀጥል ሲሆን፣ ለወደፊትም በውጭ ምንዛሪ ድልድል ረገድ በኃላፊነት በመሥራት ለሀገራችን የተረጋጋ የኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋፆ አጠናክሮ ይቀጥላል።
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button