- የዕውቅና ሽልማትም ተበርክቶለታል
አቢሲንያ ባንክ የሴፍ ላይት ኢንሼቲቭ 2025 አካል በሆነው በአዲስ አበባ በፒያሳ በቀድሞው አጠራር ፖስታ ቤት ግቢ “በክሬቲቭ ሀብ ’’ በተዘጋጀው አውደ-ርዕይ ላይ ከነሐሴ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
ይህ“የእሷ-YE’ESUA ቴክ አውደ-ርዕይ” ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የሥራ መሪዎች፣ ሴት አመራሮች፣ ሥራ ፈጣሪዎችና ሌሎች ታዳሚዎች በተገኙበት በተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ተወካይ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ኅብረት ልዩ ተወካይ በሆኑት በተከበሩ ዶሪስ ሙፑሞ በደማቅ ሁኔታ የተከፈተ ሲሆን እስከ ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡
በዕለቱም “አይ.ሲ.ቲና ዲጅታል ኢኮኖሚ የሴቶች ተጠቃሚነት” በሚል የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን ባንካችንን በመወከል በዲጅታል ባንኪንግ የኦንላይን መርቻንትና ፊን-ቴክ ማኔጅመንት ሥራ አስኪያጅ ወይ. ሰላም ጎሹ ተሳትፈዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ባንካችን በቅርቡ ያስተዋወቀውን ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት ጨምሮ ሌሎች በተለይ ሴቶችን ያማከሉ የባንክ አገልግሎቶችንና ሥራ ፈጣሪ ሴቶችን ለማበረታታት ያለመያዣ የተሰጠውን ብድር በተመለከተ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ግንዛቤ ለመፍጠር ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በዕለቱም ባንካችን ያከናወናቸውን ሴቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎች ለመንግሥት ኃላፊዎች፣ ለዓለም አቀፍ ረጂ እና አጋር ድርጅቶች ተወካዮች ገለጻ ተደርጓል፡፡
ሴፍ ላይት ኢንሼቲቭ በየዓመቱ ወጣት አመራሮችን ለማብቃት የአመራርነት ጉባኤና ወድድር (Leadership Conference and Competition) በማዘጋጀት የሚታወቅ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከጁላይ 22- 24, 2025 በተለያዩ ኩነቶች በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢ.ሲ.ኤ) በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ ይታወሳል፡፡
እ.ኤ.አ ከጁላይ 22-24, 2025 በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 5ተኛው ዓመታዊ ሊደርሽፕ ጉባኤና ውድድር ላይ አይ.ሲ.ቲ/ቴክ/ አውደ-ርዕይ፣ የወጣት ሴቶች አመራርነት ጉባኤና ውድድር፣ እንደዚሁም እ.ኤ.አ ጁላይ 31, 2025 የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች በተገኙበት ዲፕሎማሲያዊ እራት ግብዣና የዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይም የባንካችን ከፍተኛ የስራ መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ባንካችንም በዕለቱ የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡















Leave a Reply