አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/80 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ C.P.O በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ንብረቶቹ በሚገኙበት የባንኩ ቅርንጫፎችና አና ሰሜን ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ሕንፃ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር 6ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ በስም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መካሄጃ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ጨረታው በሚካሄድበቸው ቦታዎች ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በሰንጠረዥ በተገለጸው ቦታ የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 እስከ 5፡30 ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች በገዢው ይከፈላሉ። የሊዝ ክፍያ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-4594 / 0918-778427 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Leave a Reply