- የቢ.ዋይ.ዲ ሴጉል መኪና ለዕድለኛ ተዘጋጅቷል
ባንካች አቢሲንያ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በማስመልከት ለ5ኛ ጊዜ “እችላለሁ!” በሚል መሪ ቃል ከማርች 8 እስከ ኤፕሪል 8 ቀን 2026 ድረስ የሚቆይ ልዩ የሴቶች ወር መርሐ ግብር መጀመሩን ገለጸ።
የባንካችን ቺፍ ኢንተርፕራይዝ ሰርቪስ ኦፊሰር ወ/ሮ መሠረት አስፋው ትናንት የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት በተከናወነው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ይህ ዓመታዊ መርሐ ግብር አቢሲንያ ባንክ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ እና ተጠቃሚነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ ሴቶችን ለማበረታታት የታለሙ የማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን ከሽልማት ጋር አጣምሮ በያዘው በዚህ መርሐ ግብር ለሴት ስራ ፈጣሪዎች የብድር ዕድል፣ የደም ልገሳ መርሐ ግብር፣ የፋይናንስ ዕውቀት ስልጠና እና ለሴት ስራ ፈጣሪዎች ባዛር ተካትተዋል።
በተጨማሪም በቲክቶክ የፈጠራ ውድድር አዲስ ሐሳብ ላላቸው ወይም ሥራቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ሴቶች የሚሰጥ 1ኛ ለምትወጣ 500,000 ብር፣ ለ2ኛ 300,000 ብር እና ለ3ኛ 150,000 ብር የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል።
እንዲሁም የአደይ እና የዘህራህ ምርቶች የሚያስተዋወቅ ፈጠራ የታከለበት የቲክቶክ ማስታወቂያ ለሚሠሩ ሴቶች ለ1ኛ አሸናፊ 200,000 ብር፣ ለ2ኛ 150,000 ብር እና ለ3ኛ 100,000 ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።
ከሁሉም በላይ በዘንድሮው “እችላለሁ!” መርሐ ግብር ከቀደሙት ዙሮች በተለየ ሁኔታ ለአሸናፊ ሴቶች የ2025 ቢ.ዋይ.ዲ ሴጉል ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ዕድልን ይዞ መጥቷል።
ደንበኞችም የዕጣው ተሳታፊ ለመሆን አዲስ ሂሳብ በመክፈት ቢያንስ እስከ 500 ብር መቆጠብ፣ ቁጠባን ማሳደግ፣ ሳይንቀሳቀሱ የቆዩ ሂሳቦችን ማንቀሳቀስ፣ በQR ኮድ እና በP2M (ከግለሰብ ወደ ነጋዴ) የዲጂታል ክፍያዎችን መፈጸም እና ከባንካችን ጋር ከሚሰሩ ሴት ነጋዴዎች ላይ ቢያንስ የ500 ብር ግብይት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል።
በመጨረሻም ውድ ደንበኞቻችን፣ አጋሮቻችን እና መላው ሴቶች በዚህ መርሐ ግብር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ እና የዕድሎቹ ተቋዳሽ እንዲሆኑ ባንካችን ጥሪውን ያቀርባል።





Leave a Reply