bankofabyssinia.com

ባንካችን አቢሲንያ ለታላቁ ከያኒ ጌትነት እንየው  የ5 ሚሊዮን ብር ሥጦታ አበረከተ

ባንካችን አቢሲንያ ለታላቁ ከያኒ ጌትነት እንየው  የ5 ሚሊዮን ብር ሥጦታ አበረከተ

ኑ ጌትነትን እናመስግነው በሚል የሁለገቡ ከያኒ ጌትነት እንየው የ68ኛ ዓመት የልደት በአልና የ43 ዓመታት የሙያ አገልግሎት የምስጋና መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መከበሩን ተከትሎ ባንካችን አቢሲንያ ለታላቁ ከያኒ ጌትነት እንየው የብር 5 ሚሊዮን ሥጦታ አበረከተ፡፡
በዚህ ተስፋ የኪነጥበብ ኢንተርፕራይዝ ባዘጋጀው እና በርካታ የጥበብ ቤተሰበች በተገኙበት ልዩ የምስጋና መርሐ-ግብር ላይ ባንካችን አቢሲንያ ለከያኒ ጌትነት እንየው የ5 ሚሊዮን ብር ስጦታ ያበረከተ ሲሆን፣ ለአርባ ሶስት ዓመታት ለኪነጥበብ ላበረከተው ጉልህ አስተዋፅኦ ባንካችን ያለውን ክብር እና አድናቆት በመግለጽ በቅርቡ በባህርዳር ከተማ የሚከፍተውን ቅርንጫፍ በጌትነት እንየው ስም መሰየሙን ጨምሮ በዝግጅቱ ላይ ይፋ አድርጓል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ባንካችንን በመወከል ንግግር ያደረጉትና ሽልማቱን በይፋ ያበሰሩት የባንካችን ዋና- ኢንተርፕራይዝ ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ መሠረት አስፋው በባንካችን ስም ለከያኒ ጌትነት እንየው የመልካም ልደት እና ውጤታማ የስራ ዘመንን በማስታወስ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የእለቱ ክብር እንግዳ ረዳት ፕሮፌሰር- ነብዩ ባዬ ለሀገር ብዙ ውለታ የሰሩ ግለሰቦችን ማመስገን፤ ማገዝ በእጅጉ ሊበረታታ የሚገባው እና ባንካችንም ለታላቁ ከያኒ ያደረገው የእውቅና ስጦታ እና በስሙ ቅርንጫፍ መሰየም ለጌትነት የሚገባው መሆኑን አስረድተው ለባንካችን ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button