ባንካችን አቢሲንያ ትናንት ማክሰኞ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ከብር 14 ሚሊዮን በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
በዕለቱ ባንካችንን በመወከል በስፍራው የተገኙት የባንካችን ዋና የኮርፖሬት የሰው ሃብት ኦፊሰር አቶ ሰይፉ ቦጋለ በማዕከሉ ተዘዋውረው ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው የ14,488,000.00 (አሥራ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንያ ሥምንት ሺሕ) ብር የገንዘብ ድጋፉን ለማኅበሩ መሥራች እና በጎ አድራጊ አቶ ቢንያም በለጠ (የክብር ዶ/ር) አስረክበዋል።
አቶ ቢንያም በበኩላቸው ድጋፉ የበጎ አድራጎት ማህበሩ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ በሚያስፈልገው ሰዓት የተደረገ እገዛ መሆኑን ገልጸው በዚህም ባንካችን ላደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን ባንካችን አቢሲንያ በየዓመቱ ኅዳር 2 ቀን 2018 በመቄዶንያ የሚታወስ መሆኑን በመግለጽ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የባንካችን አመራሮች እና ሠራተኞች ለአረጋውያን መኖሪያ እና የህክምና ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ተደርጎ እየተሠራ በሚገኘውን ባለ 15 ወለል ዘመናዊ ህንጻ ተጠልለው ያሉና በማዕከሉ ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙ ወገኖቻችንን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ለአረጋውያኑ ልዩ የምሳ ግብዣም አድርገዋል።
በመጨረሻም ባንኩ በቀጣይም ከሰራተኞች በየወሩ ከደሞዛቸው በፈቃዳቸው ከሚያደርጉት መዋጮ ከብር 1 ሚሊዮን በላይ እየሰበሰበ ለማህበሩ ለመስጠት ቃል ገብቷል።













Leave a Reply