በፍጥነት መልኩን በመቀያየርና የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት ላይ የሚገኘው የፋይናንስ ዓለም የደንበኞች እርካታን እና የፋይናንስ አካታችነትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ መንገዶችን በየጊዜው በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ከሚሆኑ እርምጃዎች አንዱ እና ዋነኛው በቅርቡ አቢሲንያ ባንክ ለደንበኞቹ ያስተዋወቀው ገንዘብ ማስተላለፍን የተመለከተው ስር ነቀል ማሻሻል ይጠቀሳል፡፡ ይህ ስትራቴጂካዊ ውሳኔ የደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ በእጅጉ ከማሻሻሉም ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ በቀዳሚነት ከተያዙ ነጥቦች አንዱ የሆነውን የፋይናንስ አካታችነትን በማሳደግ ረገድ ወሳኝ በሚባል ደረጃ የፋይናንስ ምህዳሩን የሚያሰፋ የአሰራር ለውጥ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍም ገንዘብ ማስተላለፍን በተመለከተ በአቢሲንያ ባንክ የተደረገው ማሻሻያ ምንን እንደሚያጠቃልል፣ ደንበኞችን እንዴት ባለ አግባብ እንደሚጠቅም ብሎም በዓለም ዙሪያ ያሉ የአሰራር ስርዓቶችን ባንኩ ካስተዋወቀው አሰራር ጋር በማስደገፍ ይዳሰሳሉ፡፡
ገንዘብ ማስተላለፍን በተመለከተ በአቢሲንያ ባንክ የተደረጉ ማሻሻያዎች
በቅርቡ በአቢሲንያ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ገንዘብ ማስተላለፍን በተመለከተ የተደረገው ማሻሻያ መተግበሪያውን በመጠቀም ከአቢሲንያ ባንክ አካውንት ወደ ሌላ የአቢሲንያ ባንክ አካውንት ወዳለው ደንበኛ የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮችን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የአቢሲንያ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን በመጠቀም በሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮች ከዚህ ቀደም በአንድ ቀን ውስጥ ማስተላለፍ የሚቻለውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በተመለከተ ተጥሎ የነበረው የገንዘብ ዝውውር ገደብ ያነሳ ሲሆን ደንበኛው የገንዘብ ማስተላለፉን በሚከውንበት ወቅትም ምንም አይነት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ የማይኖር መሆኑ ሌላኛው የደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ የሚጨምር ነጥብ ነው፡፡ ይህም ደንበኞች በተሻለ የአገልግሎት ጥራት እና ያለምንም ገደብ ገንዘብ እንዲያስተላለፉ በማበረታታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለኢኮኖሚው መሳለጥ የራሱን ጉልህ አበርክቶ የሚያደርግ ነው፡፡
ማሻሻያው ለደንበኞች ምን በጎ ፋይዳ ይኖረዋል ?
1- የፋይናንስ ተደራሽነትን ይጨምራል
የገንዘብ ዝውውርን በተመለከተ በተደረገው ማሻሻያ በጉልህ ከተዳሰሱ ጉዳዮች አንዱ እና ዋነኛው የሆነው ከዚህ ቀደም ደንበኞች በሚያደርጓቸው የገንዘብ ዝውውሮች ላይ ተጥሎ የነበረው የአገልግሎት ክፍያ መነሳት በአነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የባንኩ ደንበኞች በሚያስተላልፉት ገንዘብ ላይ የሚታሰብን ተጨማሪ ክፍያ በመሸሽ ባንኮች ከሚያቀርቧቸው የፋይናንስ አገልግሎቶች እንዳይርቁ ከማድረጉም በላይ ደንበኞች በባንካችን በኩል የሚያደርጓቸው የገንዘብ ዝውውሮች ላይ የሚኖርን ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ሳያሳስባቸው በቀላሉ እና አዳዲስ ገጽታዎችን ባካተተው የአቢሲንያ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም ገንዘብ በቀላሉ ማስተላለፍ እንዲችሉ ያደርጋል፡፡
2- የፋይናንስ ተሳትፎን ያበረታታል
የፋይናንስ አካታችነት ለአንድ ሃገር የኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ከሚባሉ ነጥቦች ዋነኛው መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ በዚህ ረገድም ከዚህ ቀደም የገንዘብ ዝውውርን በተመለከተ የነበሩ በአንድ ቀን መተላለፍ የሚችል ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እና በዝውውር ወቅት የሚኖርን የአገልግሎት ክፍያ በማንሳት ብዙ ደንበኞች አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ በማበረታታት ከዚህ ቀደም በፋይናንስ ስርዓቱ ተጠቃሚ ያልነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ስርዓቱ በማካተት የራሱን አስተዋጽዖ ያበረክታል፡፡
3- የዲጂታል ክፍያን ያበረታታል
በፍጥነት እያደገ ከመጣው የዲጅታል ክፍያ ስርዓት ጋር እኩል ለመሄድ በሚያስችል አግባብ አዲሱ የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ካስተዋወቀው ፈጣን እና ቀልጣፋ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት በተጨማሪ የገንዘብ ዝውውርን የተመለከተው ማሻሻያ ደንበኞች ቀላል እና ቀልጣፋ የሆነውን የዲጂታል ባንኪንግ ዓለም ኢንዲቀላቀሉ የሚያስችል ማበረታቻ ነው፡፡ ይህም በበኩሉ ግለሰቦች በጥሬ ገንዘብ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት እንዲቀንሱ እና ኢትዮጵያ በ2025 ዓ.ም ለማሳካት ካለመችው የዲጅታል ኢትዮጲያ ስትራቴጂካዊ እቅድ ጋር ተመጋጋቢ የሆነ እርምጃ ነው፡፡ ይህም ለተለያዩ ግለሰባዊ የገንዘብ ልውውጦች በብዛት ጥቅም ላይ በመዋል ላይ የሚገኘውን የአቻ-ላቻ የገንዘብ ዝውውርን ያበረታታል (encourage peer to peer transactions) ፡፡ ይህም ደንበኞች እርስ በእርሳቸው ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ገንዘብን ያለ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ማስተላለፍ ከመቻላቸውም ባሻገር ቀላል እና ምቹ የሆነውን የአቢሲንያ ባንክን የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም በቀላሉ ግብይትን መፈጸም፣ ለተለያዩ ፍላጎቶቻቸውም ገንዘብ መላላክን በማቅለል የዲጅታል ግብይቶችን በተሻለ ቅልጥፍና እንዲፈጽሙ ያስችላል፡፡
4- የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ጥራት
መሰል የአገልግሎት ጥራት መሻሻል ላይ የሚደረጉ ለውጦች ደንበኞች የሚያገኙት አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ እና ለዕለት ተዕለት ፍላጎቶቻቸው በቂ መፍተሔን ይዞ የሚቀርብ ከመሆኑም በላይ ደንበኞች የባንክ አገልግሎቶችን በተሻለ ፍጥነት እና ጥራት እንዲያገኙ ያስችላል፡፡
ደንበኞች ማሻሻያውን እንዴት መጠቀም ይችላሉ?
ደንበኞች ከዚህ የሚከተሉትን ነጥቦች ከግምት በማስገባት በክፍያ ገደብ እና የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ የተደረጉትን ማሻሻያዎች ለመጠቀም ይችላሉ፡-
1- መደበኛ የሂሳብ ዝውውሮች፡ ደንበኞች የሚያደርጓቸውን እንደ ወርሀዊ የቤት ኪራይ፣ የጋራ መዋጮዎችን እና የአገልግሎት ክፍያዎች የመሳሰሉ መደበኛ የሂሳብ ዝውውሮችን በአቢሲንያ ባንክ የሞባይል መተግበሪያ በኩል በማድረጋቸው ብቻ ተጨማሪ ክፍያዎችን ከመቆጠባቸው በተጨማሪ ደንበኞች በቀላሉ ክፍያን በዲጅታል አማራጭ የመፈጸም ልምዳቸውንም ያዳብራሉ፡፡ ይህም ከጥሬ ገንዘብ ጥገኝነት የተላቀቀ ማህበረሰብን (cash-light society) ለመፍጠር እንደ ሀገር የተያዘውን ስትራቴጂክ እቅድ ለማሳካት የራሱን ጉልህ ድርሻ የሚወጣ ነው፡፡
2- ለአነስተኛ ቢዝነሶች የተሻለ የቁጠባ አማራጭ፡ በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች በሚያከናውኗቸው የዲጅታል ግብይቶች አልያም የገንዘብ ዝውውሮች ወቅት ስለሚኖሩባቸው ተጨማሪ ክፍያዎች ማሰባቸው የማይቀር ነው፡፡ ነገር ግን በአዲሱ የአቢሲንያ ባንክ አሰራር ለሚከውኗቸው የክፍያ ልውውጦች ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እና የክፍያ ገደብ ሳይኖርባቸው በተፋጠነ እና ወጪን በቆጠበ አግባብ የንግድ እንቅስቃሴዎቻቸውን ለመከወን ከመቻላቸውም በላይ ለአገልግሎት ይከፍሉት የነበረውን ክፍያ ለመቆጠብ ይችላሉ፡፡
3- የባንክ አገልግሎቶችን መጠቀም እንዲችሉ በር ይከፍታል፡ በተሻሻለው አሰራር ክፍያቸውን በተሳለጠ አግባብ ያለምንም ገደብ እና ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ በመከወን ላይ የሚገኙ ደንበኞች በዚህ አሰራር በመሳብ ከተለመደው በጥሬ ገንዘብ ግብይት ከመፈጸም ይልቅ ወደ ዘመናዊው እና አስተማማኙ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ ትኩረታቸውን ከማድረጋቸውም በላይ ሌሎች በዲጅታል ባንኪንግ ዘርፍ ያሉ እንደ ብድር፣ የቁጠባ አገልግሎት እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ያሉ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ በር ከፋች ነው፡፡
ከላይ በአቢሲንያ ባንክ የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያን እና የክፍያ ገደብን የተመለከቱ ጉዳዮችን የተመለከትን ሲሆን ከዚህ በመቀጠል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት በሚሰጧቸው ዲጅታል አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ አሰራሮችን እንደሚከተለው እንመለከታለን፡-
የአገልግሎት ክፍያን የተመለከቱ ዓለም ዓቀፍ የአሰራር ስርዓቶች
1- ከክፍያ ነጻ ዲጅታል ባንኪንግ
ይህ አሰራር በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው በፊን ቴክ ዘርፍ በተሰማሩ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች ወጣት እና የአገልግሎት ክፍያን የመሳሰሉ ተጨማሪ ወጪዎችን በተመለከተ ንቁ የሆኑ ደንበኞችን ለመሳብ እንደ የገበያ ሽፋንን ማስፋፊያ ዕቅድ በስፋት በመተግበር ላይ ያለ ሲሆን በዚህም ተጠቃሽ የሆነው መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ቻይም (Chime) ሲሆን አገልግሎቱን ለሚጠቀሙ ደንበኞች የትኛውንም ዓይነት የአገልግሎት ክፍያን አይጠይቅም፡፡
2- ደረጃ ያለው የክፍያ ስርዓት (Tiered Fee Structures)
ከአገልግሎት ክፍያ ስርዓቱ ስያሜ ለመረዳት እንደሚቻለው ደንበኞች ባላቸው የአገልግሎት አጠቃቀም ደረጃ ለተጠቀሙት አገልግሎት የሚከፍሉትን ክፍያ የሚወሰንበት አሰራር ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች ነባር ደንበኞችን ጠብቆ ለማቆየት ብሎም አዳዲስ ደንበኞች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ለማበረታታት የሚዘረጋ አሰራር ሲሆን በአብዛኛው የሚተገበረው በተደጋጋሚ የዲጅታል ግብይትን በሚከውኑ የሞባይል ባንኪንግ ሂሳቦች ላይ ወይም በዲጅታል የክፍያ/የገንዘብ ማስተላለፊያ ስርዓቱ በሚተላለፉ መጠናቸው ከፍ ያለ የገንዘብ ዝውውሮች ወቅት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሲንጋፖሩ ዲ.ቢ.ኤስ ባንክ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡
3- በዲጅታል የገንዘብ ዝውውሮች ላይ የሚደረጉ ማበረታቻዎች
ከላይ የተጠቀሱት አሰራሮች እንዳሉ ሆነው የተለያዩ የፊን ቴክ ካምፓኒዎች በበኩላቸው በመተግበሪያዎቻቸው ላይ በሚያልፉ የገንዘብ ዝውውሮች ላይ ክፍያን ካለመጠየቃቸውም በላይ ደንበኞች ተመላሽ አልያም ሌሎች እንደ የሽልማት ነጥብ ያሉ ማበረታቻዎችን በመጠቀም ግብይትም ሆነ ገንዘብ ማስተላለፍን በዲጅታል ዘዴ እንዲያከናውኑ የሚያበረታቱበት ስርዓት ነው፡፡
4- ማህበረሰብ ተኮር ማበረታቻዎች
እነዚህ የዲጅታል የክፍያ ስርዓትን በመጠቀም የሚከወኑ የገንዘብ ማስተላለፍ ስራዎችን በአንድ አካባቢ ላሉ የህብረተሰብ (በፋይናንስ አገልግሎት ሰጪው ለተለዩ) ክፍሎች ብቻ በተገደበ መልኩ ከአገልግሎት ክፍያ ነጻ በመሆን እንዲከወኑ በማድረግ ዕድሉ የተመቻቸለት ማህበረሰብ በአካባቢው ለሚያደርጋቸው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ጥቅም ላይ እንዲያውላቸው በተለያዩ የማህበረሰብ ዓቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሲተገበሩ ይስተዋላል፡፡
ማጠቃለያ
አቢሲንያ ባንክ የገንዘብ ዝውውር ገደብ እና የአገልግሎት ክፍያዎች በባንኩ ደንበኞች መካከል በሚደረጉ የዲጅታል ባንኪንግ የገንዘብ ማስተላለፍ ወቅት ማንሳቱ ባንኩ የደንበኞች አገልግሎት እርካታን ለመጨመር ያለውን ከፍተኛ ትኩረት ከማመላከቱም በተጨማሪ ደንበኞች የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለመጠቀም ያላቸውን ተነሳሽነት በማሳደግ የፋይናንስ ተደራሽነትን በመጨመር ለአጠቃላይ ለኢኮኖሚው ከፍተኛ አወንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አሙን ነው፡፡
በመሆኑም ደንበኞች የተሻሻለውን አሰራር በመጠቀም በቀላሉ፣ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ ብሎም ያለ ገደብ ገንዘብን በአዲሱ የአቢሲንያ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመላክ ለዕለት ተዕለት የፋይናንስ ፍላጎቶቻቸው መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ይህም አቢሲንያ ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተለዋዋጭ ከሆነው የደንበኞች ፍላጎት እኩል ለመራመድ ያለውን ተቋማዊ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡

Leave a Reply