Author: Bank of Abyssinia (Misale Solomon)

ባንካችን የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን አስመልክቶ በሁለተኛ ዙር ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም የላፕቶፕ ዕድለኛ ለሆኑት ደንበኛ ሽልማቱን አስረከበ!
Post

ባንካችን የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን አስመልክቶ በሁለተኛ ዙር ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም የላፕቶፕ ዕድለኛ ለሆኑት ደንበኛ ሽልማቱን አስረከበ!

ባንካችን በሁለተኛው ዙር 2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን አስመልክቶ ባዘጋጀው የሽልማት መርሀ ግብር የላፕቶፕ ዕድለኛ ለሆኑት ደንበኛ ዛሬ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም.  ሽልማታቸውን አስረክቧል። ባንካችን አቢሲንያ ዓለም አቀፍ የዲጂታል መክፈያ ሲስተም ከሆነው ቪዛ ጋር በመተባበር ደንበኞች የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን ተጠቅመው ግብይት ሲፈጽሙ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በቀጥታ የመመልከት ዕድል የሚያስገኝ ታልቅ የሽልማት ፕሮግራም አዘጋጅቶ እንደነበር...

የዲጂታል ግብይትና ደንበኞች ሊገነዘቧቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነጥቦች
Post

የዲጂታል ግብይትና ደንበኞች ሊገነዘቧቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነጥቦች

ከቅርብ አመታት ወዲህ በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘው የዲጂታል ግብይት ዘርፍ ብዙዎች በሚፈጽሙት ግዢ፣ ንግድ በሚከወንበት አግባብና በግብይት ወቅት በሚስተዋሉ የግብይት ዝንባሌዎችን በአዲስና ከዚህ ቀደም ባልተስተዋለ መንገድ በመቀየር አዲስ የግብይት ስርዓትን ይዞ ቀርቧል፡፡ በዚህ ረገድም የዲጂታል ግብይት ዘዴዎች በብዙዎች የዕለት ተዕለት የኑሮ ክንውን ውስጥ በዋነኛነት ይዘውት በቀረቡት ምቾት፣ ቅልጥፍናና አማራጭ አንጻር ይህ ነው የማይባል ቦታን መያዝ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአለም ዙሪያ በብዙዎች ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘውን የዲጅታል ግብይትን በቁጥሮች በማስደገፍ ስናስቀምጠው ከጠቅላላው የአለም ህዝብ 33 በመቶ የሚሆነው የዲጅታል ግብይትን የዕለት ተዕለት ህይወቱ አንድ አካል በማድረግ ግብይትን በዚሁ ስርዓት የሚፈጽም ሲሆን ይህም በአመት ከ 6.8 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይገመታል፡፡  የዲጅታል  ግብይት ምንድነው ?          ከርዕሱ ለመረዳት እንደሚችለው የዲጅታል ግብይት አማራጭ በአጭሩና ብዙሀኑን በሚያግባባ ሁኔታ ሲቀመጥ ኢንተርኔትን ማለትም ኤሌክትሮኒክ ዘዴን በመጠቀም ቁሶችን ወይም አገልግሎቶችን ለመግዛት አልያም ለመሸጥ የሚያስችል የግንኙነት ዘዴ ተብሎ ሊወሰድ ይቻላል፡፡ በመሆኑም ይህ የግብይት ዘዴ በምርት እና አገልግሎት አቅራቢ እና በደንበኛው መካከል ድልድይ በመሆን ቀላል እና ቀልጣፋ ግብይት እንዲከወን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ስለ ዲጅታል የግብይት ዘዴዎች ይህን ካልን ምን ዓይነት የዲጅታል ክፍያ ዘዴዎችን በሰፊው በጥቅም ላይ በመዋል ላይ እንደሚገኙ ከዚህ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡  1.   ነጋዴ – ለደንበኛ (B2C): በዚህ የዲጅታል ግብይት ስርዓት የተለያዩ የንግድ ተቋማት ለደንበኞቻቸው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን በቀጥታ ተደራሽ የሚያደርጉበት አሰራር ሲሆን በአለም ዙሪያ እንደ አሊባባና (Alibaba) አማዞን (Amazon) ያሉ የዲጅታል አገልግሎት ሰጪዎች በዚህ ዘርፍ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ 2.   በንግድ ተቋማት መካከል የሚደረጉ የዲጅታል ግብይቶች (B2B) ፡ ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው በዚህ ዓይነት የግብይት ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑት በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት አልያም ነጋዴዎች ሲሆኑ ለንግድ ስራቸው መከወኛ የሚያስፈሉጓቸውን ግብአትና አገልግሎቶችን በዲጅታል መተግበሪያዎች በታገዙ ዘዴዎች የሚያገኙበት አሰራር ሲሆን በአሁኑ ወቅት እንደ ቶማስ ኔት (Thomasnet) ያሉ ድረ ገጾች በአለም ዙሪያ ተጠቃሽ አገልግሎት ሰጪዎች ናቸው፡፡ 3.   ደንበኛ ለደንበኛ (C2C) ፡ እነኚህ የግብይት መፈጸሚያ ዘዴዎች በተለምዶው ደንበኞች ተብለው የሚጠቀሱት ተደራሾች እርስ በእርሳቸው ግብይት የሚፈጽሙበት ሲሆን እንደ ኢቤይ (eBay) እና ኢትሲ(Etsy) ያሉ ድረ ገጾች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ 4. ደንበኞች ለንግድ ተቋማት (C2B) ፡ ደንበኞች እንዴት ባለ መንገድ ለንግድ ተቋማት ምርት እና አገልግሎት ያቀርባሉ የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ የሚነሳ እና ከተለመደው አሰራር የራቀ ቢሆንም በዚህ ዘርፍ የሚጠቀሱት ጉዳዮች በእጅጉ ከሙያ ስራዎች ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በእጅጉ በመስፋፋት ላይ ባለው የፍሪላንስና የጊግ ኢኮኖሚ ተጠቃሽ የሆኑት አፕ ወርክ (Upwork) እና ፋይቨር (Fiverr) እንደ አብነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ 5. መንግስት ለንግድ ተቋማት (G2B): በዚህ ዘርፍ መንግስታት ለሚከውኗቸው ትላልቅ ግዢዎች ግልጋሎት ላይ የሚውሉ ሲሆኑ በሀገራችንም የመንግስት ግዢን ለመከወን የሚያስችል የዲጂታል ግብይት መፈጸሚያ ስርዓት እ.ኤ.አ 2024 ጀምሮ በስራ ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡ የዲጂታል ግብይት መፈጸሚያዎች መሰረታዊ ባህሪያት   የተገልጋዩን ምቾት ከማረጋገጥ፣ ከመረጃ ደህንነትና የአሰራር ቅልጥፍናን ማረጋገጥ ወሳኝ እና የትኛውም የዲጅታል ግብይት መፈጸሚያ ስርዓት በመመሰረታዊነት ሊያሟላ ከሚገቡት ነጥቦች መካከል ተቀዳሚ እና ዋነኞቹ ከመሆናቸውም በላይ እነዚህ መሰረታዊያን አለመሟላታቸው በአገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ መሰረታዊ የሚባል ክፍተት ማስከተሉ እሙን ነው፡፡ በዚህ ረገድ የትኞቹ መሰረታዊያን በዲጅታል ግብይት መፈጸሚያዎች ላይ በተቀዳሚነት መተግበር እንዳለባቸው ከዚሀ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡- 1- ለደንበኛ ተስማሚነት (User friendliness) ፡ የትኛውም የግብይት መተግበሪያ ግልጽ እና በቀላሉ ተጠቃሚ ሊረዳው በሚችል ብሎም አገልግሎትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማግኘት የሚያስችል መሆን ተቀዳሚው ተግባሩ መሆን ይኖርበታል፡፡ 2- ከእጅ ስልኮች ጋር ያለው ተስማሚነት፡ አብዛኞቹ የዲጂታል ግብይቶች በእጅ ስልኮች እንደሚደረጉ ብዙ ጥናቶች አመላካች ናቸው፡፡ ይህም የትኛውም ሰፊ ተደራሽነት ሊኖረው የሚፈልግ የዲጅታል ግብይት መተግበሪያ ተገልጋዮቹ በየትኛውም የእጅ ስልክ እና ቦታ ላይ ያለ ምንም የአገልግሎት መቆራረጥ ስራቸውን ለመከወን እንዲችሉ ሁኔታዎችን የሚያመቻች መሆን ይኖርበታል፡፡ 3- ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ፡ የዲጅታል ግብይቶች በየዕለቱ ከሚያስተናግዱት ትልቅ የገንዘብ መጠን እና በሚያሳልፏቸው ግለሰባዊ ባህሪ ያላቸው ልዩ የፋይናንስ መረጃዎች አንጻር ደህንነታቸው የተጠበቀና ለአጭበርባሪዎች ተጋላጭነታቸው በእጅጉ የቀነሰ መሆን ይኖርበታል፡፡ በዚህ ረገድ ከተለያዩ ምርት እና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር በመስራት ላይ የሚገኘው አቢሲንያ ባንክ ባስተዋወቀው እጅግ ዘመናዊ የደህንነት መጠበቂያ አሰራሮችን ባካተተው የባንኩ ሞባይል ባንኪንግ ፕላትፎርም በመጠቀም ደህንነትዎን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ 4- የተለያዩ የክፍያ አማራጮች፡ ደንበኞች የተለያዩ የክፍያ አማራጮችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የትኛውም የዲጅታል ግብይት አገልግሎት ሰጪ በዚህ ረገድ ለተገልጋዮቹ ምቹና ቀላል የሆኑ የክፍያ መንገዶችን በመተግበሪያው ላይ ማካተት ይኖርበታል፡፡ እዚህ ላይ አቢሲንያ ባንክ በተለያየ ጊዜ ያስተዋወቃቸውን እንደ ንክኪ አልባ የግብይት መፈጸሚያ፣ ቀላል እና ምቹ የሆነው የአፖሎ ኪው አር ኮድ እና መሰል ዘመናዊ መተግበሪያዎችን ከዲጅታል ግብይት አገልግሎቱ ጋር በማስተሳሰር ደንበኞች የተሻለ የአገልግሎት እርካታ እንዲያገኙ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ 5- ግላዊነትን መጠበቅ፡ ደንበኞች እንዳላቸው ግላዊ ፍላጎት አልያም ዝንባሌ የተመጠነ የዲጅታል ግዢ ልምድን እንዲያገኙ ለማስቻል መተግበሪያዎች በየጊዜው ራሳቸውን እያደገ ከሚመጣው የደንበኞች ፍላጎት ብሎም ደንበኛው በመተግበሪያው ወይም የግብይት ድረ-ገጹ ላይ ባለው ቆይታ በመረጠው መንገድ ግብይቱን ለመፈጸም የሚያስችለው አሰራር መዘርጋቱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ 6...

ባንካችን የ2026 ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ ለወጣላቸዉ ዕድለኞች የሽኝት መርሐ-ግብር አካሄደ 
Post

ባንካችን የ2026 ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ ለወጣላቸዉ ዕድለኞች የሽኝት መርሐ-ግብር አካሄደ 

ባንካችን “አቢሲንያ- ቪዛ 2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ” በሚል መጠሪያ ከቪዛ ጋር በጋራ ባካሄደው የሽያጭ ዘመቻ ላይ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ ለወጣላቸዉ አራት ዕድለኞች የሽኝት መርሐ-ግብር አካሄደ።  ትናንት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በባንካችን ዋና መ/ቤት በተካሄደው የሽኝት መርሐ-ግብር ላይ የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ  እንደተናገሩት እነዚህ ዕድለኞች አስፈላጊውን የጉዞ ፈቃድ ያገኙና የ2026...

የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ አክሲዮኖች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (Central Security Depository) ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ስለማሳወቅ
Post

የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ አክሲዮኖች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (Central Security Depository) ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ስለማሳወቅ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ሁሉንም አክሲዮኖች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) እና በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) በኩል የወጡ መመሪያዎችና አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሠረት አክሲዮኖቹ በኤሌክትሮኒክ መልክ በተሳካ ሁኔታ በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት (CSD) ላይ መመዝገባቸውን እንዲሁም በምዝገባው ሂደት ወደ ግምጃ ቤት (CSD) ገቢ የተደረጉ የባለአክሲዮኖች መረጃዎችና የአክሲዮን ድርሻ ትክክለኛ ስለመሆናቸው ባንካችን...

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የመጀመሪያ ዙር 4 ዕድለኞች ይፋ አደረጉ
Post

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የመጀመሪያ ዙር 4 ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸዉን የመጀመሪያ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ። መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን የዲጂታል ከስተመር አኪዩዜሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ስሜ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል። ግልጽነትን...

የባንካችን “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የሽልማት መርሃ-ግብር  የሃዩንዳይ መኪና ዕድለኛ ይፋ ሆነ
Post

የባንካችን “ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የሽልማት መርሃ-ግብር  የሃዩንዳይ መኪና ዕድለኛ ይፋ ሆነ

“ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የተሰኘው የሽልማት መርሃ-ግብር መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ላይ የሃዩንዳይ አክሰንት ሴዳን ዘመናዊ መኪና ተሸላሚ ይፋ ሆኗል። በዚህ የባንካችን ቺፍ ከስተመር ማኔጅመንት ኦፊሰር የሆኑት አቶ ደሳለኝ ይዘንጋው እና ሌሎች የባንካችን የበላይ የሥራ አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች...

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Post

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Post

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከተዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Post

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከተዉን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Post

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ /አሁን በሚገኙበት ይዞታ/ ላይ እንዳሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

Call Now Button