ከቅርብ አመታት ወዲህ በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘው የዲጂታል ግብይት ዘርፍ ብዙዎች በሚፈጽሙት ግዢ፣ ንግድ በሚከወንበት አግባብና በግብይት ወቅት በሚስተዋሉ የግብይት ዝንባሌዎችን በአዲስና ከዚህ ቀደም ባልተስተዋለ መንገድ በመቀየር አዲስ የግብይት ስርዓትን ይዞ ቀርቧል፡፡ በዚህ ረገድም የዲጂታል ግብይት ዘዴዎች በብዙዎች የዕለት ተዕለት የኑሮ ክንውን ውስጥ በዋነኛነት ይዘውት በቀረቡት ምቾት፣ ቅልጥፍናና አማራጭ አንጻር ይህ ነው የማይባል ቦታን መያዝ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአለም ዙሪያ በብዙዎች ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘውን የዲጅታል ግብይትን በቁጥሮች በማስደገፍ ስናስቀምጠው ከጠቅላላው የአለም ህዝብ 33 በመቶ የሚሆነው የዲጅታል ግብይትን የዕለት ተዕለት ህይወቱ አንድ አካል በማድረግ ግብይትን በዚሁ ስርዓት የሚፈጽም ሲሆን ይህም በአመት ከ 6.8 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይገመታል፡፡ የዲጅታል ግብይት ምንድነው ? ከርዕሱ ለመረዳት እንደሚችለው የዲጅታል ግብይት አማራጭ በአጭሩና ብዙሀኑን በሚያግባባ ሁኔታ ሲቀመጥ ኢንተርኔትን ማለትም ኤሌክትሮኒክ ዘዴን በመጠቀም ቁሶችን ወይም አገልግሎቶችን ለመግዛት አልያም ለመሸጥ የሚያስችል የግንኙነት ዘዴ ተብሎ ሊወሰድ ይቻላል፡፡ በመሆኑም ይህ የግብይት ዘዴ በምርት እና አገልግሎት አቅራቢ እና በደንበኛው መካከል ድልድይ በመሆን ቀላል እና ቀልጣፋ ግብይት እንዲከወን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ስለ ዲጅታል የግብይት ዘዴዎች ይህን ካልን ምን ዓይነት የዲጅታል ክፍያ ዘዴዎችን በሰፊው በጥቅም ላይ በመዋል ላይ እንደሚገኙ ከዚህ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡ 1. ነጋዴ – ለደንበኛ (B2C): በዚህ የዲጅታል ግብይት ስርዓት የተለያዩ የንግድ ተቋማት ለደንበኞቻቸው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን በቀጥታ ተደራሽ የሚያደርጉበት አሰራር ሲሆን በአለም ዙሪያ እንደ አሊባባና (Alibaba) አማዞን (Amazon) ያሉ የዲጅታል አገልግሎት ሰጪዎች በዚህ ዘርፍ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡ 2. በንግድ ተቋማት መካከል የሚደረጉ የዲጅታል ግብይቶች (B2B) ፡ ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው በዚህ ዓይነት የግብይት ሂደት ተሳታፊ የሚሆኑት በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት አልያም ነጋዴዎች ሲሆኑ ለንግድ ስራቸው መከወኛ የሚያስፈሉጓቸውን ግብአትና አገልግሎቶችን በዲጅታል መተግበሪያዎች በታገዙ ዘዴዎች የሚያገኙበት አሰራር ሲሆን በአሁኑ ወቅት እንደ ቶማስ ኔት (Thomasnet) ያሉ ድረ ገጾች በአለም ዙሪያ ተጠቃሽ አገልግሎት ሰጪዎች ናቸው፡፡ 3. ደንበኛ ለደንበኛ (C2C) ፡ እነኚህ የግብይት መፈጸሚያ ዘዴዎች በተለምዶው ደንበኞች ተብለው የሚጠቀሱት ተደራሾች እርስ በእርሳቸው ግብይት የሚፈጽሙበት ሲሆን እንደ ኢቤይ (eBay) እና ኢትሲ(Etsy) ያሉ ድረ ገጾች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ 4. ደንበኞች ለንግድ ተቋማት (C2B) ፡ ደንበኞች እንዴት ባለ መንገድ ለንግድ ተቋማት ምርት እና አገልግሎት ያቀርባሉ የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ የሚነሳ እና ከተለመደው አሰራር የራቀ ቢሆንም በዚህ ዘርፍ የሚጠቀሱት ጉዳዮች በእጅጉ ከሙያ ስራዎች ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በእጅጉ በመስፋፋት ላይ ባለው የፍሪላንስና የጊግ ኢኮኖሚ ተጠቃሽ የሆኑት አፕ ወርክ (Upwork) እና ፋይቨር (Fiverr) እንደ አብነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ 5. መንግስት ለንግድ ተቋማት (G2B): በዚህ ዘርፍ መንግስታት ለሚከውኗቸው ትላልቅ ግዢዎች ግልጋሎት ላይ የሚውሉ ሲሆኑ በሀገራችንም የመንግስት ግዢን ለመከወን የሚያስችል የዲጂታል ግብይት መፈጸሚያ ስርዓት እ.ኤ.አ 2024 ጀምሮ በስራ ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡ የዲጂታል ግብይት መፈጸሚያዎች መሰረታዊ ባህሪያት የተገልጋዩን ምቾት ከማረጋገጥ፣ ከመረጃ ደህንነትና የአሰራር ቅልጥፍናን ማረጋገጥ ወሳኝ እና የትኛውም የዲጅታል ግብይት መፈጸሚያ ስርዓት በመመሰረታዊነት ሊያሟላ ከሚገቡት ነጥቦች መካከል ተቀዳሚ እና ዋነኞቹ ከመሆናቸውም በላይ እነዚህ መሰረታዊያን አለመሟላታቸው በአገልግሎት አሰጣጣቸው ላይ መሰረታዊ የሚባል ክፍተት ማስከተሉ እሙን ነው፡፡ በዚህ ረገድ የትኞቹ መሰረታዊያን በዲጅታል ግብይት መፈጸሚያዎች ላይ በተቀዳሚነት መተግበር እንዳለባቸው ከዚሀ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡- 1- ለደንበኛ ተስማሚነት (User friendliness) ፡ የትኛውም የግብይት መተግበሪያ ግልጽ እና በቀላሉ ተጠቃሚ ሊረዳው በሚችል ብሎም አገልግሎትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማግኘት የሚያስችል መሆን ተቀዳሚው ተግባሩ መሆን ይኖርበታል፡፡ 2- ከእጅ ስልኮች ጋር ያለው ተስማሚነት፡ አብዛኞቹ የዲጂታል ግብይቶች በእጅ ስልኮች እንደሚደረጉ ብዙ ጥናቶች አመላካች ናቸው፡፡ ይህም የትኛውም ሰፊ ተደራሽነት ሊኖረው የሚፈልግ የዲጅታል ግብይት መተግበሪያ ተገልጋዮቹ በየትኛውም የእጅ ስልክ እና ቦታ ላይ ያለ ምንም የአገልግሎት መቆራረጥ ስራቸውን ለመከወን እንዲችሉ ሁኔታዎችን የሚያመቻች መሆን ይኖርበታል፡፡ 3- ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ፡ የዲጅታል ግብይቶች በየዕለቱ ከሚያስተናግዱት ትልቅ የገንዘብ መጠን እና በሚያሳልፏቸው ግለሰባዊ ባህሪ ያላቸው ልዩ የፋይናንስ መረጃዎች አንጻር ደህንነታቸው የተጠበቀና ለአጭበርባሪዎች ተጋላጭነታቸው በእጅጉ የቀነሰ መሆን ይኖርበታል፡፡ በዚህ ረገድ ከተለያዩ ምርት እና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር በመስራት ላይ የሚገኘው አቢሲንያ ባንክ ባስተዋወቀው እጅግ ዘመናዊ የደህንነት መጠበቂያ አሰራሮችን ባካተተው የባንኩ ሞባይል ባንኪንግ ፕላትፎርም በመጠቀም ደህንነትዎን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ 4- የተለያዩ የክፍያ አማራጮች፡ ደንበኞች የተለያዩ የክፍያ አማራጮችን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የትኛውም የዲጅታል ግብይት አገልግሎት ሰጪ በዚህ ረገድ ለተገልጋዮቹ ምቹና ቀላል የሆኑ የክፍያ መንገዶችን በመተግበሪያው ላይ ማካተት ይኖርበታል፡፡ እዚህ ላይ አቢሲንያ ባንክ በተለያየ ጊዜ ያስተዋወቃቸውን እንደ ንክኪ አልባ የግብይት መፈጸሚያ፣ ቀላል እና ምቹ የሆነው የአፖሎ ኪው አር ኮድ እና መሰል ዘመናዊ መተግበሪያዎችን ከዲጅታል ግብይት አገልግሎቱ ጋር በማስተሳሰር ደንበኞች የተሻለ የአገልግሎት እርካታ እንዲያገኙ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ 5- ግላዊነትን መጠበቅ፡ ደንበኞች እንዳላቸው ግላዊ ፍላጎት አልያም ዝንባሌ የተመጠነ የዲጅታል ግዢ ልምድን እንዲያገኙ ለማስቻል መተግበሪያዎች በየጊዜው ራሳቸውን እያደገ ከሚመጣው የደንበኞች ፍላጎት ብሎም ደንበኛው በመተግበሪያው ወይም የግብይት ድረ-ገጹ ላይ ባለው ቆይታ በመረጠው መንገድ ግብይቱን ለመፈጸም የሚያስችለው አሰራር መዘርጋቱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ 6...
Category: Blog
Why Relationship Banking Still Matters in the Digital World and BoA’s Practice
The banking industry is experiencing one of the most profound transformations in its history. Digital platforms, mobile applications, artificial intelligence and fintech innovations have reshaped how individuals and businesses access financial services. Transactions that once required face-to-face meetings can now be completed in seconds through smartphones. While this digital evolution has delivered unprecedented convenience and...
Financial Consumer Protection and Bank of Abyssinia’s Practice
Importance of Financial Consumer Protection Financial consumer protection plays a critical role in safeguarding the rights and interests of individuals who use financial services such as banking, insurance, and microfinance. In Ethiopia, the rapid expansion and increasing complexity of the financial sector have made consumer protection an important policy priority. Ensuring that customers are treated...
የደንበኞች የዲጂታል ፋይናንስ ግላዊ መረጃዎች እንዴት ይጠበቃሉ?
ለተለያዩ አገልግሎቶች ረጃጅምና አሰልቺ የይለፍ ቃላትን ለማስታወስ መሞከር ባስ ሲልም ረስቶ መንገላታት የብዙዎቻችን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ግን እየዘመነ በመጣው የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት አዳዲስ፣ ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑ የፋይናንስ ደህንነት ስርዓቶችን በማካተት እነዚህን ችግሮች መቅረፍ ተችሏል፡፡ይህም ፋይናንስንና ቴክኖሎጂን አጣምረው በመስራት ላይ ያሉ እንደ ባንክ፣ ፊንቴክ ኩባንያዎችና ሌሎች መሰል ተቋማት ከሚሰጡት አገልግሎት ጎን ለጎን በየጊዜው...
የአቢሲንያ የሞባይል ባንክ የገንዘብ ዝውውር ክፍያም ገደብም የለውም
በፍጥነት መልኩን በመቀያየርና የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት ላይ የሚገኘው የፋይናንስ ዓለም የደንበኞች እርካታን እና የፋይናንስ አካታችነትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ መንገዶችን በየጊዜው በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ከሚሆኑ እርምጃዎች አንዱ እና ዋነኛው በቅርቡ አቢሲንያ ባንክ ለደንበኞቹ ያስተዋወቀው ገንዘብ ማስተላለፍን የተመለከተው ስር ነቀል ማሻሻል ይጠቀሳል፡፡ ይህ ስትራቴጂካዊ ውሳኔ የደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ በእጅጉ ከማሻሻሉም ባሻገር በሀገር...
Bank of Abyssinia Goes Paperless Across All Branches
Bank of Abyssinia officially launched its comprehensive paperless banking services across all branches nationwide today. The inauguration took place at the newly established Ras Special Branch in Addis Ababa, chosen as a symbolic location for its modern design and strategic importance. The event was attended by key figures, including the Governor of the National Bank...
Abyssinia Bank’s Paperless Pivot Strategic Masterstroke
By: Mohammed N.Khalifa Chief International Banking Officer In a move that may redefine the contours of banking in Ethiopia, the Bank of Abyssinia (BoA) has quietly undertaken one of its most transformative operational overhauls to date. It has launched a wholesale shift to paperless banking. The decision to go paperless is not meant to be...
Say Goodbye to Paper—Experience the Future of Banking with Bank of Abyssinia!
Bank of Abyssinia marked a transformative milestone today by officially launching its innovative paperless banking service across all its branches. The groundbreaking initiative was unveiled at the state-of-the-art Ras Special Branch in a ceremony attended by National Bank of Ethiopia (NBE) Governor, Ato Mamo Mehretu, Bank of Abyssinia CEO, Ato Bekalu Zeleke, Senior Executives, bank...
9ኙ ደንበኛ ተኮር ማሻሻያዎች !
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ከግንባር ቀደሞቹ ተዋናዮች መካከል አንዱ የሆነው አቢሲንያ ባንክ እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን የዲጂታል ፋይናንስ ፍላጎት ለማርካት በስራ ላይ ያዋለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ብዙዎችን ቀልጣፋና ምቹ የሆነ አገልግሎት ባሉበት እንዲያገኙ በማስቻል ላይ ይገኛል፡፡ መተግበሪያው በስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ዘመኑን የዋጁና ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን በተግባር ላይ ያዋለ ሲሆን ይህ አጭር ጽሁፍ...
እራስዎን እንዴት ከአጭበርባሪዎች ይጠብቃሉ?
በዘመናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና የተጠቃሚዎቹን ቁጥር በእጅጉ በመጨመር ላይ የሚገኘው የዲጂታሉ አለም ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ለተጠቃሚዎች የያዘ ነው፡፡ ሆኖም ይህ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት በአገልግሎት ሰጪዎች እና ተጠቃሚዎች በቂ እና በየጊዜው የሚተገበሩ የደህንነት ጥበቃ ቅድመ ስራዎች ካልተሰራበት እጅግ ጉልህ የሆነ ኪሳራን ሊያስከትል እንደሚችልም አያጠያይቅም፡፡ ይህ አጭር ጽሁፍም በዲጂታሉ አለም እያደገ እና መልኩንም ከአዳዲስ የቴክኖሎጂ ለውጦች...








