በዴፍ ኮሚዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን የሚደገፉ መስማት የተሳናቸው ሴቶች የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመትን አስመልክተው በባንካችን ዋና መ/ቤት በመገኘት በሃገራችን የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የእንቁጣጣሽ ወይም “አበባ አየሽ ሆይ” ዜማ አቀረቡ።
እነዚህ በቁጥር አስራ ሁለት የሚሆኑ ሴቶች በሃገር ባህል ልብስ አምረውና ደምቀው ያለባቸውን የመስማት ውስንነት ወደጎን ትተው ሲወዛወዙና ሲጨፍሩ የተመልካቾችን ቀልብ በእጅጉ ገዝተውት ነበረ።
እንደሚታወቀው ባንካችን አቢሲንያ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና የማኅበረሰባችንን ችግሮች ለመቀነስ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፣ ለአብነትም ማየት ለተሳናቸው ወገኖች የሚያገለግል ባለማዳመጫ ኤ.ቲ.ኤም ስራ ላይ ካዋለ ቆይቷል፡፡
በተመሳሳይም ባንካችን መስማት የተሳናቸው ወገኖቻችን ምቹ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙና እንዲሁም በእነዚህ ወገኖቻችን ዙሪያ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ለሚገኘው ዴፍ ኮሚዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን የብር 100,000(አንድ መቶ ሺሕ) ድጋፍ አድጓል፡፡
ትናንት ጷግሜ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በባንካችን ዋና መ/ቤት በተካሄደው በዚህ ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ላይም የባንካችን ሴት አመራሮችና ሠራተኞች ታድመው ነበር።

Leave a Reply