· የአባመላ ቅርንጫፍ ደንበኛችን የባለ 2 መኝታ አፓርታማ ዕድለኛ ሆነዋል
ባንካችን አቢሲንያ ላለፉት አምስት ወራት ሲያከናውን የቆየውን በተለያዩ የዲጂታል ባንክ አማራጮች ግብይት የሚያከናውኑ ደንበኞችን የሚያበረታታ ዘመቻ (Merchant Engagement Campaign) በይፋ በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ለአሸናፊ ደንበኞች የተዘጋጀውን የመኖሪ ቤት ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።
ዕጣ የማውጣቱ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም የባንካችን የዲጂታል ባንክ ዋና ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ሶስና መንገሻና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች፣ተጋባዥ እንግዶችና ታዛቢዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዕድል አዳራሽ ተካሂዷል።
በወጣው ዕጣ መሰረትም ባለ 2 መኝታ አፓርታማ የሚያስገኘው አሸናፊ የዕጣ ቁጥር 0001801876786 ሆኖ የወጣ ሲሆን ዕድለኛውም የባንካችን አባመላ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑትና በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ መሐመድ ከድር ሆነዋል።
ይህ የሽልማት መርሃ-ግብር ይፋ ከተደረገበት ከሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አምስት ወራት ከ10 ሚሊዮን በላይ ግብይቶች የተከናወኑ ሲሆን በዚህም ከብር 138 ቢሊዮን በላይ ማንቀሳቀስ ተችሏል።
ባንካችን አቢሲንያ የዲጂታል መተግበሪያ በመጠቀም የሚደረጉ ግብይቶችን ለማበረታታትና አዳዲስ የዲጂታል ባንክ ደንበኞችን ለማፍራት ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር በሞባይል ባንክ፣በፖስ እና በሌሎች የዲጂታል አማራጮች ከብር 500 ጀምሮ ግብይት ለፈጸሙ ደንበኞች ከ3 ሚሊዮን በላይ የዕጣ ቁጥሮችን ወይም ኩፖኖችን ተደራሽ አድርጓል።
ባንካችን ዕድለኞችን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ በቀጣይም የባንካችንን እጅግ ዘመናዊ የዲጂታል ባንክአማራጮች በመጠቀም እግረ መንገዳቸውንም የተለያዩ ዕጣዎች ባለዕድል እንዲሆኑ ይጋብዛል።




Leave a Reply