የበጎነት ተግባራት ከምንግዜውም በላቀ በጉልህ በሚስተዋሉበት ታላቁ የረመዳን ወር፤ ባንካችን እየከወነው የሚገኘው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ለበጎነት የተዘረጉት የአቢሲንያ አሚን እጆች፤ እንደ ሁልጊዜውም በፆም ወቅት በቂ ማፍጠሪያ ማግኘት ለማይችሉና ለተቸገሩ ወገኖቹ በመድረስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በዚህም በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በሐዋሳ እና በዲላ ከተሞች ከሚገኙ የተራድኦ ተቋማት ጋር በመቀናጀትና ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።
የአቢሲንያ አሚን የወርሓ ረመዳን የኸይር ተግባር ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፤ በደሴ እና በኮምቦልቻ እንደዚሁም በመቀሌ ከተሞች የበጎነት አሻራውን በማሳረፍ፤ ከተቸገሩ ወገኖቹ ጎን እንደሚቆም አስመስክሯል።
አሚን ለበጎነት!








Leave a Reply