አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (የኢ.ካ.ገ.ባ) ባጸደቀው ደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና በኢ.ካ.ገ.ባ በተሰጠ ፈቃድ መሰረት፣ ከጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 3,125,000.00 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ) መደበኛ አክሲዮኖችን በአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር 1,600.00 (አንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር) ሽያጭ የሚያከናውን መሆኑን በደስታ ይገልጻል፡፡
በአቢሲንያ ባንክ ደንበኛ ሳቢ መግለጫ ላይ እንደተመላከተው ነባር ባለአክሲዮኖች ባላቸው የአክሲዮን መጠን ልክ አዲስ አክሲዮኖችን እንዲገዙ የተደለደለ ሲሆን፣ በነባር ባለአክሲዮኖች ያልተገዙ አክሲዮኖችን ተጨማሪ አክሲዮን ለመግዛት ፍላጎታቸውን ለገለጹ ለነባር ባለአክሲዮኖች የሚደለደል ይሆናል፡፡ በመሆኑም የተደለደለላችሁን አዲስ አክሲዮኖችም ይሁን በነባር ባለአክሲዮኖች ያልተገዙትን ተጨማሪ አክሲዮኖች ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ ነባር ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖቹን ለመግዛት ትችሉ ዘንድ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን እውቅና ከተሰጣቸው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አገበያዮች (ደላሎች)፣ የግብይት ሂሳብ (Trading Account) በመክፈት የአክሲዮን ግዥውን እንድትፈጽሙ ባንኩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ ባለአክሲዮኖች የሚከተሉትን አስፈላጊ ሰነዶች ይዘው ሊቀርቡ ይገባል:- (1) የፋይዳ መታወቂያ፣ (2) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ (3) የኢሜይል አድራሻ፣ (4) በተወካይ አማካይነት የሚፈጸም ከሆነ የውክልና ማስረጃ፡፡
ማሳሰቢያ፡ ባለአክሲዮኖች ደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ፤ ለውሳኔ የተቸገሩ ከሆነ በኢ.ካ.ገ.ባ ፍቃድ ከተሰጣቸው ገለልተኛ የፋይናንስ አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ፣ የደንበኛ ሳቢ መግለጫው መጽደቅ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ባለሃብቶች እንዲገዙ የተሰጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (የኢ.ካ.ገ.ባ) ፈቃድ አግኝቷል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ ለገሐር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07፣ ጋምቢያ መንገድ በአካል ቀርቦ ማናገር ወይም በስልክ ቁጥር፡ +251-115-526314/0974-506535/0911-373294/0937-439882 መደወል ይችላሉ፡፡
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.

Leave a Reply