ቆጠብ ያሸልማል” እና የሦስተኛ ዙር የ“እንሸልምዎ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

ቆጠብ ያሸልማል” እና የሦስተኛ ዙር የ“እንሸልምዎ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

አቢሲንያ ባንክ ደንበኞቹን ለማበረታታት የተለያዩ የሽልማት ስጦታዎችን እያዘጋጀ ከዘርፉም የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ይታወሳል፡፡ ይኽንን ተከትሎ የሁለተኛ ዙር “መቆጠብ ያሸልማል” እና የሦስተኛ ዙር የ“እንሸልምዎ” ፕሮግራም ታህሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ተጀምሮ ነሐሴ 13 ቀን 2013 ዓ.ም መጠናቀቁን ተከትሎ የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ተካሂዷል፡፡ባንካችን በሁለቱም መርሐ ግብር በድምሩ 225 የሽልማት አይነቶች ያቀረበ ሲሆን በውጭ ምንዛሪ (በእንሸልምዎ) መርሃ ግብር 43 የእጣ አይነቶች ከ1ኛ —8ኛ እጣ የተዘጋጀ ሲሆን እንዲሁም በሀገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብ (መቆጠብ ያሸልማል) መርሃ ግብር ደግሞ 182 የሚሆን የሽልማት አይነቶች አዘጋጅቷል፡፡በመሆኑም በድምሩ 225 ለሆኑት የሽልማት አይነቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት በትናንትናው እለት መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ የተካሄደ ሲሆን፤ ባንካችን በዕጣ የተለዩ ዕድለኞቹን በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች በዝርዝር የሚያሳውቅ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button