ባንካችን አቢሰንያ ለመጀሪያ ጊዜ የፀረ- ሙስና ቀንን “ በስነምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በሀገር ደረጃ የሚከበረውን በዓል በካፒታል ሆቴል አክብሮ ዋለ

ባንካችን አቢሰንያ ለመጀሪያ ጊዜ የፀረ- ሙስና ቀንን “ በስነምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በሀገር ደረጃ የሚከበረውን በዓል በካፒታል ሆቴል አክብሮ ዋለ

ሙስና ለመላው አለም ሀገራት ህዝቦች አለመረጋጋት፣ ሰላም እጦት፣ የልማት ኋላቀርነት፣ ለዲሞክራሲ አለመዳበርና የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ለሠብአዊ መብት ጥሰት፣ ለአየር መዛባትና ለስደት ከሚዳርጓቸው የጋራ ምክንያቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡

በዚህ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቁ የአለማችን ህዝቦች ውስጥ አህጉራችን አፍሪካ ግንባር ቀደም ስትሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም በዚህ አደገኛ ችግር ሠለባ ከሆኑት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ትጠቀሳለች፡፡

ይህን አለማቀፋዊ የሀገራት ህዝቦች የጋራ ችግር በጋራ ለመዋጋትና ለመከላከል እንዲያስችል በማሰብ የተባበሩት መንግስታት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን እ.ኤ.አ በ 2003 በሜክሲኮ “ሜሪዳ” በአባል ሀገራት ፀድቆ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም ከፈራሚና አፅዳቂ ሀገራት አንዷ ስትሆን ይህንኑ ስምምነት እ.ኤ.አ ህዳር 26/2007 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወጣው አዋጅ ቁጥር 544/1999 በማፅደቅ የሀገሪቱ የህግ አካል በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን አከናውናለች፡፡ እያከናወነችም ትገኛለች፡፡

በ1987 ዓ.ም በወጣው የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 9(4) መሰረት የኢትዮጵያ የምታፀድቃቸው አለምቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ የህግ አካል ተደርጎ እንደሚወሰድ የሚደነግግ በመሆኑ ይህም ስምምነት በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሀገሪቱ የህግ አካል ሆኖ በአስገዳጅነት ህግ ተደንግጓል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ስምምነት ውሳኔ መሠረት ቀኑ በአባል ሀገራት በየአመቱ እንዲከበር በተወሰነው መሠረት ዘንድሮ ማለትም በ2014 ዓ.ም በአለም ዐቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ “ በስነምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

በመሆኑም በሚያዝያ 2013 ዓ.ም የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1236/2013 በተሸሻለው ህግ መሰረት ህዝባዊ ድርጅቶች የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ክፍል እንዲያቋቁሙና ከኮሚሽን ፅ/ቤቱ ጋር አብረው እንዲሰሩ ይደነግጋል፤፤ በዚሀም መሰረት ባንካችን የአዋጁን ድንጋጌ ተከትሎ ወደ ስራ በመግባቱ ክፍሉን ከማቋቋም ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን በጅምር ደረጃ እየሰራና ወደፊት ከኮሚሽን ፅ/ቤቱ ጋር በጋራ ለመስራት እቅድ አስቀምጧል ይህ ዛሬ የምናከብረው እለት የዚህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button