ባንካችን አቢሲንያ የእችላለሁ መርሐ ግብር አሸናፊ የሆኑ እንስቶችን ሸለመ

ባንካችን አቢሲንያ የእችላለሁ መርሐ ግብር አሸናፊ የሆኑ እንስቶችን ሸለመ

ባንካችን አቢሲንያ ማርች 8 አስመልክቶ ለ3ተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የእችላለሁ መርሐ ግብር በድምፅና በቲክ ቶክ አጭር ቪዲዮ ከ1-3 ደረጃን ላገኙ እንስቶች እንዲሁም በሥራ ፈጠራ ተወዳድረው አሸናፊ ለሆኑ እንስቶች ለሥራ ማስፋፊያ የሚሆን በአነስተኛ ወለድ ያለዋስትና ብድር ያመቻቸበት ፕሮግራም በዛሬው እለት ተጠናቀቀ፡፡

የባንካችን ማህበራዊ ኃላፊነት አንድ አካል በሆነው በዚህ ዝግጅት አደይ እና ዘሀራ (ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑ እንስቶች) የሴቶች ቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶቹን ከዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ጋር በማያያዝ ሰፊ የማስተዋወቅ እና የሽያጭ ዘመቻዎችን ያከናወነ ሲሆን፣ ዘመቻው በመላው ሀገራችን የሚገኙ እንስቶችን እንዲያሳትፍ ተደርጓል፡፡ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 8-31 ባሉት ቀናት ውስጥ በድምፅ፣ በቲክ ቶክ አጭር ቪዲዮ እና በሥራ ፈጠራ ለመወዳደር ፍላጎቱ ያላቸው እንስቶች የመወዳደሪያ ሥራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ የተደረገ ሲሆን፣ በዘርፉ አንቱ በተባሉ ባለሞያዎች እና ከሕዝብ በተሰበሰበ ድምጽ አሸናፊዎች እንዲለዩ ተደርጓል፡፡

በዚሁ የሽልማት መርሐ-ግብር ላይ ከማየት ውሱንነት ጋር የሚኖሩ የሰባት ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሦስት መንታ ሕፃናትን በተደራራቢ ችግሮች ውስጥ እያሳደገች ያለችው ጀግና እናት ወ/ሮ ትዕግስት ካሳ በክብር እንግዳነት እንድትገኝ የተደረገ ሲሆን፡- እነዚህ ሕጻናት የውጭ ሕክምና ቢያገኙ የማየት እድላቸው ሰፊ እንደሆነ በቅድመ ምርመራ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ ከተጠየቀው ከፍተኛ የሕክምና ወጪ አኳያ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግሞችን እያካሄዱ የሚገኙ ሲሆን፣ ባንካችን አቢሲንያም የዚህችን ጠንካራ እናትና የሕጻናት ልጆቿ የወደፊት ሕይወት ቀና እንዲሆን ካለው ጽኑ ፍላጎት በመነሳት የበኩሉን ድጋፍ ማድረጉ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በእጅጉ እንዲወጣ የሚያደርገው በመሆኑ ለውጭ ሀገር የሕክምና ወጪያቸው የሚያግዛቸውን የብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) ድጋፍ አድርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button