ባንካችን አቢሲንያ ትናንት መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በዲጂታል ክፍያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ከሆነው ቪዛ ጋር የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።
ይህ ስምምነት የክፍያ ስርዓትን ለማዘመን፣ ከጥሬ ገንዘብ አልባ ግብይቶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ሁለቱ ተቋማት በሃገራችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና አካታች የዲጂታል ክፍያ መፍትሄዎችን (Solutions) ለማስፋፋት ያላቸውን የረጅም ጊዜ የጋራ ቁርጠኝነት ያጠናክራል።
የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ “ይህ የዛሬው ስምምነት ለደንበኞቻችን የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማሳደግ በምናደርገው ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው!” ብለዋል።
ወ/ሮ ሶስና ንግግራቸውን በመቀጠል “ከቪዛ ጋር ያለንን ትብብር በማጠናከር በመላ ሃገራችን ላሉ ግለሰቦች፣ የንግድ ተቋማት እና ነጋዴዎች እያደገ የመጣውን ፍላጎት የሚያሟሉ አስተማማኝ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና አዳዲስ የክፍያ መፍትሄዎችን (Solutions) የማቅረብ አቅማችንን እያጎለበትን እንሄዳለን” ብለዋል።
በቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ክላስተር ኃላፊ አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው “የኢትዮጵያ ገበያ አስፈላጊ እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያለ በመሆኑ፣ ቪዛም የዲጂታል ክፍያ ምህዳሩን ዕድገት ለመደገፍ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ ነው” ብለዋል።
“ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ያለን ዘላቂ ትብብር ፈጠራን እና የፋይናንስ አካታችነትን በመደገፍ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ የክፍያ ስርዓት ለመፍጠር ያለመ ነው” ሲሉም አክለዋል።





Leave a Reply