አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዕጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/71/2019 እና የባንኩ ባለአክሲዮኖች ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም. 26ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባፀደቀው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና ምርጫ ማስፈፀሚያ የአሠራር ደንብ መሠረት ነው፡፡

በዚህ መሠረት በቀጣይ ባንኩን በዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የሚያገለግሉ አባላትን ለማስመረጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራውን መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሯል፡፡

የተቋቋመው የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ጥቆማዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በመሆኑም ባለአክሲዮኖች ለባንኩ ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ብቁ ዕጩዎች ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ እንዲጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ተወዳዳሪ ዕጩዎች ማሟላት ያለባቸው አነስተኛ መስፈርት፡-

1.የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ፤

2.በዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤

3.እድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣

4.የማንኛውም ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ፤

5.የቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ፤

6.ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ወይም ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም እኩል የትምህርት ደረጃ ያጠናቀቀ፤

7.በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ አባል፣ ዳይሬክተር እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ያልሆነ፣

8.በቂ ስንቅ/ገንዘብ/ ሳይኖረው ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፤

9.ታማኝ ፤ሀቀኛ፤ ጠንቃቃና መልካም ስነምግባር ያለው፤

10.ከመመረጡ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም በሌላ ሀገር በንግድ ማህበር አደራጅነት፣ ዳይሬክተርነት፣ ሥራ አስኪያጅነት፣ ተቆጣጣሪነት፣ ኦዲተርነት ወይም በሌሎች የሥራ ኃላፊነቶች ሲሠራ በዕምነት ማጉደል፣ በሥርቆት፣ በውንብድና ወንጀል ጥፋተኛ ያልተባለ፣

11.በራሱ ወይም በሚመራው ድርጅት ላይ የመክሰር ውሳኔ ያልተሰጠበት፤ በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያነት ያልተወሰደበት፤

12.ሌሎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ መስፈርቶችን የሚያሟላ

ማሳሰቢያ፡-

1.በተባዕታይ ጾታ የተገለጠው ለአንስታይ ጾታም ያገለግላል፡፡

2.ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን መጠቆም የምትፈልጉ ባለአክሲዮኖች ለጥቆማ የተዘጋጀውን ቅጽ ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለገሀር በሚገኘው  የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 14ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 ወይም በባንኩ ሌሎች ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት መሙላት የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹን በተጨማሪነት በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ.   ድረ-ገጽ www.bankofabyssinia.com የሚገኝ መሆኑን እንገልጣለን፡፡

3.ጠቋሚዎች በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ 14ኛ ፎቅ ላይ ወይም በባንኩ ቅርንጫፎች በግንባር በመቅረብ ቅፁን ሞልታችሁ ለመመለሳቸው ማስረጃ እንዲሆን የቅጹን ኮፒ በማስቀረት ማስረከብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

4.ጠቋሚው ድርጅት ወይም ማህበር ከሆነ ቅፁን ሲሞላ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለበት፡፡

5.ከነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11: 00 ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913-17-47-16 ወይም 0911-25-73-21መደወል  ይችላሉ፡፡

የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላ እና አስመራጭ ኮሚቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button