አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን (AFCON 2021 Campaign) ምክንያት በማድረግ ላዘጋጃቸው ሽልማቶች ሁለተኛ ዙር የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ አካሄደ!

አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር የቶታል ኢነርጂስ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን  (AFCON 2021 Campaign)  ምክንያት በማድረግ  ላዘጋጃቸው ሽልማቶች ሁለተኛ ዙር የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ  አዳራሽ  አካሄደ!

አቢሲንያ ባንክ ከቪዛ ካርድ ጋር በመተባበር የካርድ ግብይትን ከፍ ማድረግ ይቻል ዘንድ በሁለት ዙር የሚጠናቀቅ የሽልማት መርሐ ግብር አዘጋጅቶ የመጀመሪያ ዕጣ አሸናፊዎች ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ አካሂዶ ዕድለኞቹ መሸለማቸው ይታወሳል፡፡ አሁንም በሁለተኛ ዙር የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ አዲስ ለወሰዱ ደንበኞቻችን እና በባንካችን ፖስ ማሽን ለተጠቀሙ ደንበኞች ከታኅሣሥ 18 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የቆየው የሽልማት መርሐ ግብር መጠናቀቁን ተከትሎ የተለያዩ ሽልማቶችን ያካተተው መርሐ ግብር ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ የባንካችን የሥራ ሃላፊዎች፤ የብሄራዊ ሎተሪ ታዛቢዎች በተገኙበት እጣው ወጥቷል፡፡

ባንካችን በሁለቱም ዙር በድምሩ 158 የሽልማት አይነቶች በማቅረብ በመጀመሪያው የካሜሩን ጉዞ የሽልማት እና ሽኝት መርሃ ግብር ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም የተከናወነ ሲሆን በሁለተኛው ዙር መርሐ ግብር ደግሞ 156 የሽልማት አይነቶች አዘጋጅቷል፡፡

በመሆኑም በድምሩ 156 ለሆኑት የሽልማት አይነቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት በዛሬው እለት የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ የተካሄደ ሲሆን፤ ባንካችን በዕጣ የተለዩ ዕድለኞቹን በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች በዝርዝር የሚያሳውቅ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button