የባንካችን ሐዋሳ ዲስትሪክት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የብር 1.3 ሚሊዮን የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ።
መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በዞኑ ዋና ከተማ አርባ ምንጭ በተከናወነው የድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባንካችን ሐዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ቦቸሬን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የጋሞ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽንና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ገዛኻኝ ጋሞና ሌሎች የስራ ሐላፊዎች ተገኝተዋል።
የባንካችን ሐዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ቦቸሬ “በዞኑ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ የባንኩ ኃላፊዎችና ባልደረቦች ልባዊ ኅዘን የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው ከሐዋሳ ዲስትሪክት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የብር 1 ሚሊዮን የጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የብር 300 ሺህ የአይነት ድጋፍ አበርክተናል” ብለዋል።
የጋሞ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ እና የብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኻኝ ጋሞ በበኩላቸው አቢሲንያ ባንክ ከሕዝብና መንግሥት ጎን በመቆሙ አመስግነዋል።





Leave a Reply