በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  • ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ግብር በዋጋ ላይ የሚታሰብ ሲሆን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ባንኩ ካለ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳ ደግሞ ወደ አሸናፊው/ገዢ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡
  • በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
  • በተራ ቁጥር 5 ፣ 6 እና 7 ለተገለጸው የጨረታው ቦታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ሲሆን ከተራ ቁጥር 1-4 የተገለጹት አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ህብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ጎን ካለው አልፓውሎ ህንጻ 3ኛ ፎቅ በባንኩ ህግ መምሪያ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-150711 እና 0115 54 67 37/36 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
 የተበዳሪው ስምከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ       የመያዣ ስጪው ስምየንብረቱ ዓይነትና አገልግሎትየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር ጨረታው የሚካሄድበት ቀን  የምዝገባ ሰዓትየጨረታ ሰዓት
    1አቶ ዘነበ ተክሉእስከ መጋቢት 18 ቀን 2012ዓ.ም ድረስ           ብር 1,285,708,49  ተበዳሪውመኖሪያ ቤት200 ካ.ሜ756/243/2002በኦሮ/ብ/ክ/መ ሰንዳፋ ከተማ ቀበሌ 01938,917.41ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡30-5፡30  5፡30-6፡00
  2    ዘመን የቴሌኮም ምርት መሸጥ ኃ/የተ/የግ/ማ    እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2013ዓ.ም ድረስ           ብር 246,805,271.01  አቶ ጸጋዬ ገ/ጻዲቅለድርጅት/ንግድ የሚሆን ህንጻ      500 ካ.ሜAA000060802064አዲስ አበባ      ቦሌ ክ/ከተማ    ወረዳ 08 1     114,315,894.00ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡30-5፡30  5፡30-6፡00
    3አቶ ይስሃቅ ሽፋሬእስከ ታህሳስ 17 ቀን  2012ዓ.ም ድረስ           ብር 63,416,341.31  አቶ ዘመኑ አበበለት/ቤት አገልግሎት የተሰሩ ቤቶች(ለትምህርት)  31,100 ካ.ሜ217/1089/2000በኦሮ/ክ/መንግስት ሰንዳፋ ከተማ   ቀበሌ 01  19,174,543.09ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡30-5፡30  5፡30-6፡00
    4  አቶ ደመቀ ንጉሴለኢንዱስትሪ    6,000 ካ.ሜ211/142/2008በኦ/ክ/መንግስት ሰንዳፋ ከተማ   ቀበሌ 0115,471,039.38ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም 8፡30-9፡30 9፡30-10፡00
  5 አቶ አለማየሁ ብርሃኔ  በየነእስከ መጋቢት 15      ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ብር 21,481,153.96ተበዳሪውህንጻ (ለፋብሪካ የተገነባ)10,000 ካ.ሜ33630/09በ/አ/ክ/መ ባህር ዳር ጣና ክ/ከተማ፤ ቀበሌ 1621,186,045.00  ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡30-5፡305፡30-6፡00
    6አቶ አሳዬ ጓዱ ጌቴእስከ ሐምሌ 24 ቀን 2011 ዓ.ም       ብር 2,111,588.67አቶ ሽባባው ታደሰመኖሪያ ቤት  270 ካ.ሜ295/2002ቻግኒ ከተማ፤  ቀበሌ 012,955,988.00ግንቦት 24 ቀን       2013 ዓ.ም4:30-5:30 5:30-6:00
  7አቶ አብርሃም ስሜእስከ ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ     ብር 1,302,004.47  ወ/ሮ ዮርዳኖስ ፍቃዱመኖሪያ ቤት  105 ካ.ሜ1056/2000ኦሮ/ክ/መንግስት አዳማ ከተማ፣  ቀበሌ 141,067,094.00   ግንቦት 11 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡30-5፡30  5፡30-6፡00
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button