ባንካችንና ቪዛ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የ3ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ አደረጉ።

ባንካችንና ቪዛ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የ3ኛ ዙር ዕድለኞች ይፋ አደረጉ።

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በስፍራው በአካል ተገኝተው ለመከታተል የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸዉን የሶስተኛ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ። መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበበ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል። በወጣው ዕጣ መሠረትም 2 የባንካችን የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ደንበኞች (የዕጣ ቁጥር 500010553 እና 000023676 ) ፣ 1 የምዕራብ አዲስ ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 900030682) እና 1 የሃዋሳ ዲስትሪክት ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 900033744) በድምሩ 4 የባንካችን ደንበኞች ዕድለኞች ሆነዋል። በዚህ የሽያጭ ዘመቻ ጠንካራ የደንበኞች ተሳትፎ የታየ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ8,600 በላይ ኩፖኖች የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርዶችን በመጠቀም ከ1,000 ብር በላይ ግብይቶችን ለፈጸሙ ደንበኞች ተልከዋል። ይህ የሽያጭ ዘመቻ በባንካችን እና በቪዛ መካከል በመላው ኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓቶችን ፍጥነት፣ ደህንነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ትብብር አካል ነው። ተጨማሪ ዕጣዎች በቀሪዎቹ ሳምንታት በሚኖሩ ቀጣይ ዙሮችም የሚወጡ ሲሆን፣ ይህም ለደንበኞች በየዕለቱ የቪዛ ካርድ ሲጠቀሙ የዓለም ዋንጫ ታዳሚ የመሆን ዕድል የሚሰጥ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button