ባንካችን አቢሲንያ የተሟላ የዲጂታል የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ አቢሲንያ ሬሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ (ሐዋላ አገልግሎት)፣ የዲጂታል የውጪ ምንዛሪ ሂሳብ ለመክፈት የምንገለገልበት ፕሮዳክት እና የአቢሲንያ ዓለም አቀፍ ቨርቹዋል ካርዶችን በይፋ አስመረቀ።
ትናንት መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ እንደተናገሩት እነዚህ ፕሮዳክቶች የውጭ ምንዛሪ ተደራሽነትን ለማሻሻል፣ የገቢ ፍሰትን መደበኛ ለማድረግ እና ብሔራዊ የፋይናንስ ስርዓቱን ለማዘመን ያስችላሉ ብለዋል።
ወ/ሮ ሶስና የዲጂታል ዘርፍ ለባንካችን ያለውን የጎላ ጠቀሜታ ሲገልጹ “ለአብነትም በዘንድሮው በጀት አመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም በዲጅታል ቻናሎቻችን የተዘዋወረው የብር መጠን ከብር 2.2 ትሪሊዮን በላይ ሆኖ ተመዘግቧል። ከባንካችን አጠቃላይ ትራንዛክሽን ወይም ግብይት አንጻር 84 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል ቻናሎቻችን አማካኝነት የተከናወነ መሆኑን ስንመለከት በዘርፉ ያስመዘገብነው እድገት ለተጨማሪ አዳዲስ ዕድሎችም በር ከፋች መሆኑን ያሳያል” ብለዋል።
ወ/ሮ ሶስና አክለውም ባንካችን የኢኮኖሚ መረጋጋትን በመደገፍ እና የውጪ ምንዛሪን በመደበኛ የባንክ ስርዓት ውስጥ በማቆየት በዲጂታል አገልግሎት ግንባር ቀደም ሆኖ መጓዙን ይቀጥላል ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል።
የባንካችን ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር አቶ ዳንኤል ሐይሉ በበኩላቸው አነዚህን ፕሮዳክቶች ለማቅረብ ባንካችን ከበስተጀርባ በርካታ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የተጠቀመ እና ሲታሰብበት የቆየ ሲሆን፣ አሁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲፈቅድ ወዲያው ሞክረን ወደ ገበያ አቅርበናቸዋል ብለዋል።
እነዚህ ፕሮዳክቶች አቢሲንያ ሬሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ (ሃዋላ አገልግሎት)፣ የዲጂታል የውጪ ምንዛሪ ሂሳብ ለመክፈት የምንገለገልበት ፕሮዳክት እና የአቢሲንያ ዓለም አቀፍ ቨርቹዋል ካርዶች ሲሆኑ ደንበኞች የውጭ ምንዛሪ እንዲልኩ፣ እንዲያስተዳድሩ እና እንዲጠቀሙ የሚያስችሉ ናቸው።
ፕሮዳክቶቹን በተመለከተ ለታዳሚያን የተደረገ ገለጻና የተለያዩ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች ለዝግጅቱ ድምቀት የሰጡ ሌሎች ሁነቶች ነበሩ።
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባንካችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የቪዛና ማስተር ካርድ ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።















Leave a Reply