ባንካችን አቢሲንያ በጅማ ከተማ በአብዱልከሪም አባገሮ (ፔሌ) ስም አዲስ ቅርንጫፍ ከፈተ

ባንካችን አቢሲንያ በጅማ ከተማ በአብዱልከሪም አባገሮ (ፔሌ) ስም አዲስ ቅርንጫፍ ከፈተ

የባንካችን ጅማ ዲስትሪክት መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በአቶ አብዱልከሪም አባገሮ (ፔሌ) ስም በጅማ ከተማ በተለምዶ ፈረንጅ አራዳ አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ቅርንጫፍ ከፈተ።

ቅርንጫፎቹን በሃገር ባለውለታዎች በመሰየም የሚታወቀው ባንካችን ከዚህ ቀደም የጅማ ከተማ ቆርቋሪ በሆኑት በንጉሥ አባጅፋር ስም ቅርንጫፍ የከፈተ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የሳቸዉ አራተኛ ትውልድ በሆኑት  አብዱልከሪም አባገሮ (ፔሌ) በከተማዋ 10ኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል።

በ1952 ዓ.ም በጅማ ከተማ የተወለዱት አብዱልከሪም አባገሮ በኢትዮጵያ ተስፋ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በመጫወት ስማቸው በጉልህ የሚወሳ ሲሆን፣ “ፔሌ” የሚለውን የቅጽል ስም ያገኙትም በወቅቱ በነበራቸው ድንቅ የእግር ኳስ ብቃት ምክንያት ነበር። 

አቶ አብዱልከሪም የአምስቱ ጊቤ ታሪክ አባት በመባል ሲታወቁ፣ በተለይም የሰላም አምባሳደር ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ”የጂማው ማህተመ ጋንዲ” ሲሉ ይጠሯቸዋል።

አቶ አብዱልከሪም  በልማት፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በታሪክና ባህል ዘርፎች በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በማከናወን ለጅማ ከተማ ብሎም ለሃገራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የጅማ ከተማ የሰላም አምባሳደር በመሆን በተለያዩ ተቋማት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

በመርሃ ግብሩ ላይም የጅማ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የባንካችን ከፍተኛ የሥራ ሐላፊዎች፣ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button