bankofabyssinia.com

9ኙ ደንበኛ ተኮር ማሻሻያዎች !

9ኙ ደንበኛ ተኮር ማሻሻያዎች !

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ከግንባር ቀደሞቹ ተዋናዮች መካከል አንዱ የሆነው አቢሲንያ ባንክ እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን የዲጂታል ፋይናንስ ፍላጎት ለማርካት በስራ ላይ ያዋለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ብዙዎችን ቀልጣፋና ምቹ የሆነ አገልግሎት ባሉበት እንዲያገኙ በማስቻል ላይ ይገኛል፡፡ መተግበሪያው በስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ዘመኑን የዋጁና ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን በተግባር ላይ ያዋለ ሲሆን ይህ አጭር ጽሁፍ ባንኩ በቅርቡ በአዲስ መልክ ለደንበኞቹ ይፋ ያደረገው የተሻሻለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ምን ዓይነት አዳዲስና ምቹ ገጽታዎች (features) እንደያዘ  የሚያትት ይሆናል፡፡

1.     የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን በሁሉም የዲጂታል መገልገያዎች ላይ

ከዚህ በፊት ስልክዎት ጠፍቶ ወይንም ተሰርቀው የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎትን ለማግኘት በአዲሱ ስልክዎት ላይ እንደ አዲስ መመዝገብ እንዳለብዎት ተነግሮት ያውቃል? አቢሲንያ ባንክ ይህን አይነቱን እንግልትና የመረጃዎች መጥፋትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚሰናበቱበትን አሰራር ይዞ መቅረቡን ብንነግሮትስ?  በተሻሻለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ አካውንታቸውን ከሚጠቀሙበት የትኛውም  የዲጂታል መገልገያቸው ላይ የአገልግሎት ይለፍ ቃላቸውን ብቻ በማስገባት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህም አገልግሎቱን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በቀላሉ ተደራሽ  የሚያደርገው ሲሆን ለደንበኞችም የተሻለ የአጠቃቀም አማራጭን ይዞ ብቅ ያለ ነው፡፡

ልዩ ልዩ ጥቅሞች

ምቾት፡ ለምን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ለማግኘት በአንድ የዲጂታል መገልገያ ማለትም ምዝገባዎን ለመጀመሪያ ግዜ በፈጸሙበት የእጅ ስልክዎ ላይ ብቻ ጥገኛ ይሆናሉ? ይልቁንም በየትኛውም ቦታ በእጅዎ ላይ የሚገኘውን የትኛውንም የዲጂታል መገልገያ በመጠቀም ዘርፈ ብዙ የፋይናንስ አገልግሎትን ካሉበት ሆነው በምቾት መጠቀም ይችላሉ፡፡

የፋይናንስ አካታችነት፡ እንደ ኢትዮጲያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ መሄድ ያለባቸውን ያህል ርቀት እንዳይሄዱና ከዘርፉ ኢኮኖሚያቸው ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም ማግኘት እንዳይችሉ ከሚያደርጉ ችግሮች አንዱ የሞባይል ስልኮች በበቂ ሁኔታ አለመዳረስ ነው፡፡ የተሻሻለው መተግበሪያ ግን ይህን ችግር በሚፈታ አግባብ የተለያዩ ደንበኞች የዲጂታል ባንኪንግ አካውንታቸውን በተመሳሳይ ስልክ ለመጠቀም የሚያስችል አሰራርን አስተዋውቋል፡፡

ደህንነትዎ በአስተማማኝ ሁኔታ ይጠበቃል፡ በአዲሱ መተግበሪያ የስልክዎ መጥፋት ወይም መሰረቅ የፋይናንስ ደህንነትዎን አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የሚጠብቁ  የምዝገባና የአገልግሎት ደህንነት መጠበቂያዎችን ያካተተ በመሆኑ በሌላ የዲጂታል መገልገያ ላይ አዲስ የይለፍ ቃል በማስገባት ያለምንም  የደህንነት ስጋት አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ፡፡

ከላይ ያየነው የተሻሻለውና በሁሉም የዲጂታል መገልገያዎች ላይ መጠቀም የሚያስችለው አሰራር በአገልግሎት ጥራት፣ ተደራሽነትና አካታችነት ላይ የራሱን ጉልህ ሚና በመጫወት የደንበኞችን እርካታ ብሎም ታማኝነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ታዲያ እርስዎስ ምን ይጠብቃሉ? ፈጥነው የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በማውረድ ፈጣንና ምቹ አገልግሎቶችን በእጅ ስልክዎ ያለ ሀሳብ ይጠቀሙ፡፡

2.    ብዝሃነት በአፖሎ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ84 በላይ ቋንቋዎች መኖራቸው የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ከእንግሊዝኛ ውጭ በሃገራችን በሰፊው የሚነገሩትን እንደ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ እና ሶማሊኛ ያሉትን ብዙ ተናጋሪ ያላቸውን የሃገራችንን ቋንቋዎች በስራ ላይ ያዋለ ሲሆን ደንበኞች ከእነዚህ አማራጮች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን በመምረጥ በተቀላጠፈና ግልጽ በሆነ አግባብ መተግበሪያውን ለመጠቀም ያስችላቸዋል፡፡

        ልዩ ልዩ ጥቅሞች

ተደራሽነት፡ ደንበኞች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲጠቀሙ ትልቅ እድል ይዞ ከመቅረቡም ባሻገር ሃገራችን የያዘችውን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ዕቅድ እንዲሳካም የራሱን ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው፡፡

ተአማኒነት፡  ደንበኞች አፋቸውን በፈቱበትና በቀላሉ በሚረዱት ቋንቋ አገልግሎት ማግኘታቸው ከሌሎች እንደ እንግሊዘኛ ባሉ ዓለም-አቀፍ ቋንቋዎች አገልግሎት ከሚሰጡ መተግበሪያዎች በተሻለ ተአማኒነት እንዳላቸውና ለመጠቀምም እንደሚዘወተሩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

ብዝሃነትን ማስተናገድ፡ የተሻሻለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ባንካችን ለመላው ኢትዮጵያውያን ተደራሽና ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ሲሆን ሃገራችን በቋንቋዎች ያላትን ብዝሃነት ከግምት ባስገባ መልኩ መተግበሪያው የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡

የቋንቋ አካታችነትን በተመለከተ በቅርቡ በአለም ባንክ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው  ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ጉዳዮች ለፋይናንስ አካታችነት በጉልህነት ከሚጠቀሱ መሰናክሎች አንዱና ዋነኛው ሲሆን ጥናቱ እንደሚያመለክተው ተቋማት በተገልጋዮቻቸው የአፍ መፍቻ ቋንቋ የተዘጋጁ አገልግሎቶችን ማቅረባቸው እንደ እንግሊዘኛ ያሉ አለም አቀፍ ቋንቋዎች በማይነገሩባቸው አካባቢዎች ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ለኢኮኖሚያዊ አካታችነት የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡

3ክፍያዎን በቀላሉ

የተሻሻለውን መተግበሪያ በመጠቀም የሚደረጉ ግብይቶችና ከባንክ ወደ ባንክ የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮች ለወትሮው ከሚፈጁት ግዜ እንዲሁም ክፍያዎቹ በተገቢው መልክ ስለመደረጋቸው የሚገልጹ ማሳወቂያዎችን  ከሚመለከተው ባንክ ለመቀበል የሚወስደውን ጊዜ ለማሳጠር ባንካችን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያውን  ከኢት-ስዊች ጋር ያስተሳሰረ ሲሆን ይህም ሪል ታይም ግሮስ ሴትልመንት (RTGS) የተባለውን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ የባንካችን ደንበኞች በስልካቸው መተግበሪያውን በመጠቀም ከባንክ ወደ ባንክ የሚያደርጉትን የገንዘብ ዝውውር በእጅጉ የሚያቀል አሰራር ነው፡፡

–        ኢትስዊች (EthSwith) ደንበኞች ለሚፈጽሟቸው ከ100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በታች ላሉ የገንዘብ ዝውውሮች

–        ሪል ታይም ግሮስ ሴትልመንት (RTGS) – ደንበኞች ለሚፈጽሟቸው ከ100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ላሉ የገንዘብ ዝውውሮች

–        ጥቅሞች፡

–        ፈጣንቀላል፡ ደንበኞች የሚያደርጓቸውን የገንዘብ ዝውውሮች በተቀላጠፈና ምቹ በሆነ አግባብ ክፍያው ለታሰበው አላማ በወቅቱ እንዲውል ያደርጋል፡፡

–        ገንዘብ ቆጣቢ፡ የኢትስዊች ዝቅተኛ የአገልግሎት ክፍያ በደንበኞች ለሚከወኑ አነስተኛ የገንዘብ ዝውውሮች ፈጣንና ወጪ ቆጣቢ አማራጭ ነው፡፡

–        ግልጽ፡ ግልጽ የሆኑት የአሰራር ደንብና መመሪያዎች ደንበኞች በግምት ላይ ተመስርተው የፋይናንስ ውሳኔዎችን እንዳያሳልፉ ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡

ደንበኛ-ተኮር የአገልግሎት ስርዓት፡ የተሻሻለው መተግበሪያ በስራ ላይ ያዋላቸው እንደ ዩዘር ኤክስፒሪያንስ ኦፕቲማይዜሽን (UX) ያሉ ገጽታዎች ደንበኞች በመተግበሪያው ላይ ባላቸው ቆይታ የተሻሉና ምክንያታዊ ውሳኔዎችን ለመወሰን እንዲችሉ የሚያስችል ገጽታ ሲሆን ይህም በአሁን ሰዓት በአለም ላይ ባሉ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በመስጠት ላይ ባሉ ተቋማት በሰፊው በተግባር ላይ የዋለ ነው፡፡

4.     ግልጽ የአገልግሎት ክፍያ ተመን

ደንበኞች ስለሚያወጧት እያንዳንዷ ሳንቲም ማሰባቸው ትክክልና የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ ተቋማትም በዚህ ረገድ ከደንበኞቻቸው ስለሚሰበስቧቸው የአገልግሎት ክፍያዎች ግልጽና ተአማኒ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የአቢሲንያ ባንክ ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ክፍያን ወደ ሌሎች ባንኮች ብሎም እንደ ኤም-ፔሳና ቴሌብር ካሉ ቴሌኮም መር የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ለሚደረጉ ግብይትና ክፍያዎች ደንበኞች ምን ያህል ብር ለአገልግሎት ክፍያ እንደተቆረጠባቸው በግልጽ እንዲመለከቱ የሚያስችል አሰራርን አስተዋውቋል፡፡

ግልጽነት ለምን?

የደንበኞች  እምነት፡ በአቢሲንያ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ የሚጠቀሙ ደንበኞች ከእውቅናቸው ውጭ ከሂሳባቸው ተቀናሽ የሚሆን ምንም ዓይነት ገንዘብ አይኖርም፡፡

የህግ ተገዥነት፡ ግልጽ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ ታሪፍ ተግባራዊ መደረግ ለደንበኞች የተሻለና ተዓማኒ አሰራርን ከማስተዋወቁም ባሻገር ባንኩ በዘርፉ ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ግልጽነት ከተደነገጉ ድንጋጌዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ስራውን ለማከወን ያለውን ዝግጁነትና የህግ ተገዢነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

የፋይናንስ ዕቅድ፡ ደንበኞች መተግበሪያውን በመጠቀም ማድረግ ለሚፈልጉት ግብይት ወይም የገንዘብ ዝውውር ምን ያህል የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ እንደሚከፍሉ ማወቃቸው የሚፈጽሟት እያንዳንዷ ግብይት በቂ በሆነ እውቀትና በዕቅድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ይረዳል፡፡

አለማቀፍ የፋይናንስ ተሞክሮ፡ በአለም ዙሪያ በፋይናንስ ማማከር ዘርፍ ካሉ ግንባር ቀደም ተቋማት አንዱ የሆነው ማኬንዚ የሰራው ጥናት እንዳሳየው 67 በመቶ የሚሆኑ የአገልግሎት ተጠቃሚዎች በዲጂታል ባንኪን የሚያደርጓቸውን ግብይቶች የአገልግሎት ክፍያዎችን ምክንያት በማድረግ እንደሚተው ያመላክታል፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተው ተቋማት ግልጽ የሆኑ የአገልግሎት ታሪፎችን በማስተዋወቅ ደንበኞች በተሻለ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ብሎም ዘላቂ ተአማኒነትን ለመገንባት እንደሚችሉ ያትታል፡፡ 

5.     በቀላሉ የሚረጋገጡ ደረሰኞች

አቢሲንያ ባንክ አዲስ ባስተዋወቀው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው በስራ ላይ ያዋለው በቀላሉ የሚረጋገጡ ደረሰኞች በሚላኩበት አሰራር (Verifiable Receipt Functionality or VRF) መሰረት ደንበኞች ግብይታቸውን ተከትሎ የሚደርሳቸው ደረሰኝ ህጋዊና ከሚመለከተው ተቋም ስለመውጣቱ የሚያረጋግጡበት አሰራር ነው፡፡ በመሆኑም አሰራሩ በየዕለቱ መጠኑ ከፍ ያለ ግብይትን በዲጂታል ባንኪንግ ለሚከውኑ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች በቀላሉ የግብይት ደረሰኞችን ህጋዊነት ለማረጋገጥና ራሳቸውን ከመጭበርበር ለመከላከል የሚረዳ ነው፡፡

በቀላሉ የሚረጋገጡ ደረሰኞች የሚላኩበት ሂደት  እንዴት ይሰራል?

ደንበኞች ገንዘብ ካስተላለፉ በኋላ ገንዘብ ላኪው መተግበሪያው ደረሰኝ እንዲያዘጋጅላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ መተግበሪያው በቀላሉ ሊረጋገጥ የሚችል እና ህጋዊ ደረሰኝ ወዲያውኑ ያዘጋጃል፡፡

ጥቅሞች፡

ግጭቶችን ያስቀራል፡ ህጋዊና በፍጥነት ሊረጋገጥ የሚችል ደረሰኝን በማቅረብ በንግዱ ማህበረሰብና በደንበኞች መካከል የሚኖር ጥርጣሬንና ቅራኔን በእጅጉ የሚቀንስ ነው፡፡

ንግድን ያፋጥናል፡ በንግዱ ዘርፍ ያሉ ደንበኞች በቀላሉ ሂሳብ ለመቀበልና ደረሰኝ በማግኘት በተሻለ ፍጥነትና ጥራት ስራቸውን እንዲከውኑ ያስችላል፡፡

ፈጣንና ቀላል፡ ደንበኞች ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ የሚመጡባቸውን እንደ ደረሰገኝ ላክልኝ ያሉ ተደጋጋሚ ምልልሶችን ያስቀራል፡፡

አለማቀፍ የፋይናንስ ተሞክሮ ፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ጥሬ ገንዘብ በሰፊው በሚንቀሳቀስባቸው ኢኮኖሚዎች ዲጂታል ደረሰኞች የተለመደውንና ረዥም ጊዜ የሚወስደውን አሰራር በመቀየር ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ የተለያዩ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ በሪፖርቱ ላይም የደረሰኝ ማጣሪያ (receipt verification) አሰራር ተአማኒና ግልጽ አሰራርን ከማሳደግ፣ ከአካታችነትና አዳዲስ የንግድ ዘርፎችን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ወሳኝ ሚና እንዳለው ያሳያል፡፡

6.    የግብይት መረጃ ስነዳ

የተሻሻለው መተግበሪያ የደንበኞችን መረጃ በአግባቡና በወጥነት ከመሰነድ አንጻር ያስተዋወቀው ወጥ የግብይት መከታተያ አሰራር (standardized transaction data presentation) ደንበኞች የግብይት መረጃቸውን በወጥነት እንዲመለከቱና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ በር የሚከፍት ነው፡፡

ለምን ይጠቅማል?

ግልጽነት፡ ደንበኞች ከዚህ በፊት ቅሬታ ሲያነሱባቸው የቆዩባቸውን እንደ የግብይት ታሪክ ወጥነት መጓደል የመሳሰሉ በአገልግሎት አሰራር ላይ ሲስተዋሉ የቆዩ ክፍተቶችን ግልጽ በሆነ አሰራር የሚቀይር ነው፡፡

ለሂሳብ ስራ ምቹነት፡ አፖሎን በመጠቀም ግብይት የሚቀበሉ ንግድ ቤቶች የንግድ ልውውጥ ያደረጉባቸውን ክንውኖች በቀላሉ ሂሳብ ለመስራትና በመካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ የሂሳብ መዛነፎችን የሚቀንስ አሰራርን ያስተዋውቃል፡፡

ስህተትን በእጅጉ ይቀንሳል፡ በመተግበሪያው የሚጠቀሙ ደንበኞች ወጥ ባልሆነ የግብይት የኋላ ታሪክ በመነሳት ሊደርሱበት ከሚችሉት የተሳሳተ ድምዳሜ በመታደግ አሁን ላይ ስላሉበት የሂሳብ ቁመና የተሟላ እውቀት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡

የግብይት መረጃ ስነዳ ንድፍ መሰረታዊ ነጥብ፡ በዚህ ረገድ አቢሲንያ ባንክ በመተግበሪያው ላይ ይህን አሰራር ማስተዋወቁ ባንኩ በደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል፡፡ በኔልሰን ኖርማን ግሩፕ የተደረገው ጥናት ይህንን በሚያጠናክር መልኩ የግብይት ታሪክ ወጥነት በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ያሉ መተግበሪያዎች በደንበኞች ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት በእጅጉ እንደሚያሳድግ ያሳያል፡፡

7.    አየር ሰዓት በቀላሉ ለመሙላት

የአየር ሰዓት ለመሙላት የሚፈልጉትን ስልክ ቁጥር በመፈለግ ጊዜ መውሰድና እሱን ተከትሎም የሚደርስ የአገልግሎት መቋረጥ ሰልችትዎታል? የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ መፍትሄ አለው፡፡ አዲሱ መተግበሪያ ባካተተው አሰራር መሰረት ደንበኛው የአየር ሰዓት ለመሙላት በራሱ የሚፈልገውን ስልክ ከማስገባት ይልቅ ካሉት የስልክ ዝርዝሮች (phone contacts) ከመተግበሪያው ጋር በቀላሉ በመገናኘታቸው በተቀላጠፈ መንገድ የአየር ሰዓቱን ለመሙላት የሚፈልገውን ስልክ በመምረጥ በምቾት የሚፈልገውን ለማከናወን የሚረዳው ነው፡፡

ለምን ይጠቅማል?

ፍጥነት፡ ደንበኛው ስልክ ቁጥሮችን አስታውሶ ከመጻፍ ይልቅ በፍጥነት ከመተግበሪያው ጋር ከተገናኘው የስልክ ዝርዝሮች (phone contacts) የሚፈልገውን ስልክ ቁጥር ለመምረጥ ይችላል፡፡

ስህተት አልባ መሆኑ፡ በስልክ ቁጥር በመሙላት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስህተቶችን የሚያስቀር ነው፡፡

ምቾት፡ በየጊዜው ለወዳጅ ዘመድ  የሞባይል ካርድ ስንሞላ በፍጥነትና በምቾት ለማከናወን ይረዳናል፡፡

ገበያው እንዴት ይቀበለዋል?

በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ባለው የሞባይል ስልክ ተጠቃሚነት አሃዝ ከአጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍል 50 ከመቶ ያለፈ ሲሆን  አፖሎ ተግባራዊ ያደረገው ይህ የአየር ሰዓትን የተመለከተው አሰራር የደንበኞች እርካታን ከመጨመር ባለፈ በዘርፉ ባሉ ሌሎች ተቋማት አሁን ላይ የሚሰራበትን ዘመናዊ አሰራር የሚያስተዋውቅ ነው፡፡

8.    የችግሮች ልየታ (Error Mapping)

ቅድመ መፍትሄዎችን በማስቀመጥ ረገድ የተሻሻለው መተግበሪያ ያካተተው የየችግሮች ልየታ (Error Mapping) አሰራር በመተግበሪያው ላይ በግብይት ወቅት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በፍጥነትና ግልጽ በሆነ አግባብ ለደንበኛው የሚያሳይ አሰራርን ይዞ ቀርቧል፡፡ ለምሳሌ በመተግበሪያው የተላከ ገንዘብ በተለያዩ ምክንያቶች ለታለመለት ዓላማና ግለሰብ ተደራሽ ባይሆን ፣ ላኪው ይህንን ሊረዳው በሚችለው አግባብ የሚከታተልበት አሰራር ነው፡፡

–        ደንበኞችን ማብቃት፡ ደንበኞች በመተግበሪያው ላይ ስለሚያደጓቸው እንቅስቃሴዎችና ስለሚከሰቱ ችግሮች በቂ መረዳት ኖሯቸው ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ እንዲያበጁ ይረዳል፡፡

–        አላስፈላጊና ጊዜ የሚወስዱ የስልክ ጥሪዎችን ይቀንሳል፡ በአብዛኛው ጊዜ የሚስተዋሉና ወደ ባንኮች የጥሪ ማዕከላት የሚደረጉ ነገር ግን ግልጽ በሆኑ መረጃዎች ሊወገዱ የሚችሉና የጥሪ ማዕከላትን ከመጨናነቅ የሚታደግ ነው

–        ግልጽነት፡ ደንበኞች የሚጠቀሙት መተግበሪያ ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ጉድለቶችን እንዲረዱና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይረዳል፡፡

 9.    የመተግበሪያው አሰራርንና የግብይት ወሰንን በተመለከተ የተደረጉ ማሻሻያዎች

በማናቸውም መተግበሪያዎች ላይ እንደሚስተዋሉት የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጀመሪያ በስራ ላይ በዋለባቸው ጊዜያት የተለያዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች ተስተውለውበት የነበረ ቢሆንም ተሻሽሎ በስራ ላይ በዋለው መተግበሪያ ላይ እነኚህ ነገሮች በጉልህ ተሻሽለዋል፡፡ ለአብነትም በተመግበሪያው ሲጠቀሙ የቆዩ ደንበኞች የሚያነሷቸውን እንደ ድንገተኛ የአገልግሎት መቋረጥ የመሳሰሉ በደንበኞች እርካታ  ላይ ጫና የሚፈጥሩ ጉድለቶች በመተግበሪያው ላይ ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፡፡

በዚህ ረገድ ደንበኞች በመተግበሪያው ላይ ከፍተኛ የአገልግሎት ፍሰት ባለባቸው ሰዓታትም ጭምር ያልተቆራረጠ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል፡፡ ይህም በመተግበሪያው ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ደንበኞች በአቢሲንያ ባንክ ደንበኝነታቸው እንዲቆዩ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ነው፡፡

በአጠቃላይ ከላይ በዋነኛነት የተመለከቱት ባንኩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ ያካተታቸው ዘጠኙ ማሻሻያዎች አቢሲንያ ባንክ በዲጂታል ባንክ ተደራሽነት እና ቀልጣፋ አሰራር ዘርፍ ጠብቆ ያቆየውን የደንበኞች እርካታ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ  ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችሉት ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button