የአቢሲንያ ባንክ የባለ አክሲዮኖች 24ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ

የአቢሲንያ ባንክ  የባለ አክሲዮኖች 24ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተካሄደ

የአቢሲንያ ባንክ የባለአክሲዮኖች 24ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ኅዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢንተርኮንትኔንታል አዲሰ ሆቴል ተካሂዷል፡፡የጠቅላላ ጉባዔው በተመደበላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከመጀመራቸው በፊት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች ቀርበዋል፡፡ከእነዚህም መካከል በዘጋቢ ፊልም የቀረበ የባንኩ የ25 ዓመታት ጉዞ ሲሆን መስራች የአክሲዮን ባለቤቶች፣ ድርጅቱን በቦርድ አባልነት ያገለገሉ፣ በባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ያገለገሉ እንደሁም አሁንም በማገልገል የሚገኙ፣ ነባር የድርጅቱ ሠራተኞች ምስክርነታቸውን እና አስተያየታቸውን የሰጡበት ነበር፡፡ በሌላ በኩል በባንኩ የ25 ዓመታት ጉዙ ውስጥ የተመዘገቡ ስኬቶችን፣ ያጋጣሙ ተግዳሮቶችን እና በማኅበራዊ ኃላፊነት የተወጣቸውን ተግባራት ያካተተ ዘገባ ነበር፡፡

በመቀጠል ምልዐተ-ጉባዔው መሟላቱን ከተረጋገጠ በኋላ የጉባዔውን አጀንዳ በማጽደቅ የዕለቱ መርሐ-ግብር ተጀመሯል፡፡ ሲያገለግሉ የቆዩ የቦርድ አባላት የአገልግሎት ዘመን በመጠናቀቁ አዲስ የቦርድ አባላትን ለመምረጥ ድምፅ ቆጣሪዎች ተሰይመው ምርጫው ተከናውኗል፡፡ በመቀጠል የዲሬክተሮች ቦርድን እንዲሁም የውጭ ኦዲተሮችን የ2019/2020 ዓመታዊ ሪፖርት እና የሒሳብ ዘመን ሪፖርት ያዳመጠው ጉባዔ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ጥያቄ በማቅረብ እና አስተያቶችን በመስጠት የተሳተፈ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቀዎች የሚመለከታቸው የቦርድ ኣባላት እና የባንኩ የሥራ አስፈፃሚዎች በቂ ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የዕለቱ ጉባኤ መርሐ-ግብር መጨረሻ የነበረው የዲሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርትን ማዳመጥና ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ባንኩን የሚያገለግሉ የቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን ሲሆን ዘጠኝ አባለት የሚገኙበትን የዲሬክተሮች ቦርድ በመምረጥ የዕለቱን መርሐ-ግብር በተሳካ መልኩ አጠናቋል፡፡ 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button