bankofabyssinia.com

ባንካችን አቢሲንያ በሁሉም ቅርንጫፎቹ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ባንካችን አቢሲንያ በሁሉም ቅርንጫፎቹ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ


ባንካችን አቢሲንያ በዛሬው ዕለት በአዲስ መልክ በተዋቀረው የባንካችን ራስ ልዩ ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ፣ የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የበላይ የሥራ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎቱን በይፋ አስመርቆ ስራ አስጀምሯል።
ይህ አዲስ አሠራር ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ጥሬ ገንዘብ ማስገባትና ማውጣት፣ ሒሳብ መክፈትና ሌሎች በቅርንጫፍ በኩል የሚሰጡ ማናቸውንም አገልግሎቶች በራስ አገዝ ወይም በሠራተኞች በመታገዝ ደህንነቱ በተጠበቀና ፈጣን በሆነ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡
አገልግሎቱ ስማርት ኪዮስኮችንና ታብሌቶችን እንዲሁም የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀም ሲሆን፣ ጊዜ የሚወስዱ የአሠራር ሂደቶችን በማስወገድ የባንካችንን የአገልግሎት ደረጃ ፈጣን፣ አስተማማኝና ግልጽ ከማድረግ አኳያ ጉልህ ለውጥ የሚያመጣ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ደንበኞች ወረፋ መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው ፈጣን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የጥሬ ገንዘብ መቀበያና መክፈያ /Recyclers/ እና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ለመቀበል የሚያስችሉ ማሽኖች /Bulk Deposit Machines/ በተመረጡ ቅርንጫፎች የተዘጋጁ ሲሆን፣ በቀጣይም በሁሉም ቅርንጫፎች ተደራሽ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
አገልግሎቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራዊ የቋንቋ አማራጮች ማለትም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በሱማሊኛ፣ በትግሪኛ፣ በአፋርኛና በሲዳምኛ የቀረበ ሲሆን፣ ሁሉንም ደንበኞች ማዕከል ባደረገ መልኩ የዕድሜ፣ የትምህርት ደረጃ ወይም ሰዎች ለቴክኖሎጂ ባላቸው የክህሎት መጠን የማይገደብ፣ ቀላል፣ አመቺና ተስማሚ ተደርጎ የቀረበ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button