ባንካችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

ባንካችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

የባንካችን የበላይ የሥራ አመራሮች ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ጊቢ በመገኘት የተቋሙን 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባንካችንን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመወከል በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የባንካችን ቺፍ ክሬዲት ቢዝነስ ኦፊሰር አቶ አሳምነው ደርበው “እንኳን ለ80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችሁ አደረሳችሁ!” ካሉ በኋላ እንደ እስካሁኑ ሁሉ በቀጣይም የሃገራችን ኩራት ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለንን ግንኙነት የበለጠ አጠናክረን እንጓዛለን ብለዋል። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው ለተደረገላቸው መልካም ምኞት አመስግነው፣ ከባንካችን ጋር አሁን ላይ ያለው መልካም ግንኙነት ወደፊትም የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።

ባንካችን በቅርቡ ባካሄደው እና ረጅም ጊዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞቹን እና አጋሮቹን በሸለመበት የደንበኞች የዕውቅና እና የምስጋና ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕውቅና ከተሰጣቸው ተቋማት መካከል አንዱ እንደነበር የሚታወስ ነው።

Call Now Button