ባንካችን አቢሲንያ በተጠናቀቀው የ2025/26 በጀት ዓመት ከፍተኛ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ ይህም ከዕቅዱም ሆነ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር ትልቅ ብልጫ የታየበት ሆኗል።
በበጀት ዓመቱ አስቸጋሪና ፈታኝ የኢኮኖሚና የቢዝነስ ተግዳሮቶች ተከስተው የነበረ ቢሆንም እንኳን፣ ባንካችን ከዕቅዱም ሆነ ካለፈው በጀት ዓመት የተሻለ ተቀማጭ ገንዘብ በመሰብሰበ የአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡን መጠን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ችሏል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ፕሮዳክቶችን እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፉ አዳዲስ የአገልግሎት መስጫ አውታሮችን እንዲሁም ፈጣን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ እጅግ ዘመናዊ የወረቀት አልባ ቅርንጫፎችን ዕውን ማድረግ ተችሏል።
በአጠቃላይ መመዘኛዎች የ2025/26 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት አንጻር ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑ ባንካችን የተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ባንካችን አቢሲንያ ለተገኘው ከፍተኛ ውጤት አስተዋጽዎ ያደረጉ አካላትን ሁሉ እያመሰገነ በዘንድሮው በጀት ዓመት የታየው ጠንካራ የሥራ ተነሳሽነት በመጪው ዓመትም የሚቀጥል ይሆናል።
