ድረ-ገጽ ባይኖርዎትም የሽያጭዎን ክፍያ መንገድ እንዴት ዲጂታል ማድረግ ይችላሉ?!

ድረ-ገጽ ባይኖርዎትም የሽያጭዎን ክፍያ መንገድ እንዴት ዲጂታል ማድረግ ይችላሉ?!

አቢሲንያ የዲጂታል ደረሰኝ መላኪያና ክፍያ መቀበያ መንገድ/Digital Invoicing Solution

በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ፣ በዲጂታል ክፍያ የተለያዩ ግብይቶች ይፈጸማሉ፡፡ የዲጂታል ክፍያ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች ኢ-ኮሜርስ የዲጂታል ንግድ ዋነኛው ነው፡፡ ኢ-ኮሜርስ ማንኛውንም ግዢና ሽያጭ በበይነ መረብ (Internet) አማካይነት ማከናወን የሚያስችል የንግድ ሥርዐት ነው።

አቢሲንያ በዲጂታል ክፍያ ግንባር ቀደም ከሆነው ከቪዛ ጋር የዲጂታል ንግድን (E-Commerce) ለማቀላጠፍ የሚያስችለውን የቪዛ ሳይበር ሶርስ Visa SyberSource Payment Gateway Technology የኦንላይን ክፍያ አማራጭ በማቅረብ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ የቀዳሚነት ሥፍራን ይዟል። በዚኽም በአገራችን ካሉ ባንኮች በቀዳሚት፣ ዘመን ከወለዳቸው ቴክኖሎጆዎች ጋር ራሱን በማላመድ የዲጂታል ንግድን በኢ-ኮሜርስ የክፍያ አማራጭ አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረ ከ1 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡

ባንካችን የዲጂታል ንግድን የሚያቀላጥፍ የክፍያ አማራጭ E-Commerce payment gateway ቴክኖሎጂን ለደንበኞቹ በማቅረብ የአገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍ ላይ ነው፡፡ E-Commerce payment gateway  ድረ-ገጽን (website) ወይም መተግበሪያዎችን (App) በመጠቀም በቪዛ አልያም በማስተር ካርድ ኦንላይን ክፍያዎችን መፈጸም የሚያችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በተለያዩ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ተቋማት፤ በውጪ አገር ያሉ ደንበኞቻቸው አቢሲንያ payment gateway የክፍያ አውታር ጋር ዌብ ሳታቸውን ወይም መተግበሪያቸው በማገናኘት ከመላው ዓለም በኦን ላይ ክፍያዎችን የሚቀበሉበት ሥርዐት ነው፡፡ በዚህም አቢሲኒያ በአገራችን የግብይት ሥርዐቱን ፍትሐዊ በማድረግ ረገድ ነጋዴውን ከሸማቹ፤ ሸማቹን ከነጋዴው ጋር በቀጥታ በማገናኘትና በመሐል ያሉ ደላሎችን የሚያስቀር ዘመናዊ ግብይትን በመፍጠር ለአገራችን ዘመናዊ የግብይት ሥርዐት ታላቅ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ነው።

እነሆ አሁን የምሥራች፤ በውጪ አገር ለሚገኙ ኦንላይን ክፍያ መፈጸም ለማይችሉ ደንበኞቻቸውና ድረ-ገጽ እና መተግበሪያ የሌላቸው ሆቴሎች፣ የጉዞ ወኪልና የአስግብኚ ድርጅቶች በቀጥታ ደንበኞቻቸው የአገልግሎት ክፍያ የሚፈጽሙበትን ዐዲስ አሠራር ዘርግቷል።

ይህ አዲስ አገልግሎት አጠቃቀሙ ምን ይመስላል?

አቢሲንያ የአገልግሎት ሒሳብ መጠየቂያ አማራጭ (Abyssinia Digital Invoicing Solution) ይሰኛል፤ የኢኮሜርስ ክፍያ አገልግሎትን ድረ-ገጽ ወይም መተግበሪያ ለማይጠቀሙ የአስጎብኚ ድርጅቶችና ሆቴሎች እንዲሁም አገልግሎቱን የሚጠቀ ሌሎች ድርጅቶች የሒሳብ መጠየቂያ ደረሰኝ ለደንበኛቻቸው አዘጋጅተው በመላክ ደንበኛው ባለበት ቦታ ሁኖ በቪዛ ወይም በማስተር ካርድ ክፍያ እንዲፈጸም የሚያስቸለ አማራጭ ነው፡፡

  • አገልግሎት አቅራቢው ደንበኛው የሚፈልገውን ዝርዝር መረጃ በሟሟላት የሒሳብ መጠየቂያዎቹን ያዘጋጃሉ፤
  • የተሞላው የሒሳብ መጠየቂያ Link በቀላሉና በፍጥነት ለደንበኛው ይላካል፤
  • ሊንኩ ለደንበኛዎ በኢሜል፣ በዋትስ አፕ፣ በአጭር የጽሑፍ መልእክት አልያም በቴሌ ግራም ሊላክ ይችላል፤
  • ደንበኛውም መልእክቱ እንደደረሰው የሊንኩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቪዛ ወይም ማስተር ካርዳቸውን በመጠቀም ክፍያውን ይፈጽማሉ፡፡

ከ Abyssinia Digital Invoicing solution ምን ያተርፋሉ?

  • በከፍተኛ ሁኔታ ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ መንገድ መሆኑ
  • ከስሕተት የጸዳ በቀላሉ የሒሳብ መጠየቂያ እንዲያዘጋጁ ያስችሎታል፤
  • የእጅ በእጅ ክፍያን በማስቀረት ጉልበትዎን፣ ጊዜዎንና ገንዘብዎን ይቀንሰሉ፤
  • ኋላ ቀር አሠራርን በማስቀረት የክፍያ መጠያቂዎችን በፖስታ ቤት በመላላክ የሚወስደውን ጊዜና ለኅትመት የሚወጣውን ወጪ ያስቀራሉ፤
  • የመረጃ አመዘጋገብ ሥርዐትን (Records Management) ና የሒሳብ ቁጥጥርዎን (Auditing) ያቀለዋል፤
  • ድረ-ገጽ ወይም መተግበሪያዎችን ሳይጠቀሙ ደንበኛዎትን በቅርበት እንዲያገኙ ያስችሎታል።

Abyssinia Digital Invoicing solution ለእርስዎ ለደንበኞችዎ በጣም ቀላል አማራጭ!

አቢሲንያ ከዘመን ጋር ተጓዠ፤ ከዘመን ጋር ደራሽ!

ምኒልክ ብርሃኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button