bankofabyssinia.com

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ባንካችን ለሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ባንካችን ለሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ
  • ለአዕምሮ ህሙማኑ የምሳ ግብዣም አድርጓል

ባንካችን አቢሲንያ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ታህሳስ 27፣ 2018 ዓ.ም ለሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር የ500 ሺህ ብር ድጋፍና በማዕከሉ ተጠልለው ለሚገኙ ህሙማን የምሳ ግብዣ አደረገ።

ባንካችንን በመወከል በስፍራው የተገኙት የመካከለኛው አዲስ አበባ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ብሩክ  አለማየሁ ድጋፉን ለሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር መስራችና ዋና ስ/አስኪያጅ አቶ ሚኪያስ ለገሰ አስረክበዋል።

አቶ ብሩክ ድጋፉን ካስረከቡ በኋላ እንደተናገሩት አቢሲንያ ባንክ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ያለው ቁርጠኝነት በየጊዜው በሚያደርጋቸው መሰል ድጋፎች የሚገለጽ ሲሆን ዛሬም የተደረገው ድጋፍ የዚሁ አካል ነው ብለዋል። አቶ ብሩክ ‘’ዛሬ ተዘዋውረን ባየነው ነገር ልባችን ተነክቷል፤ እናም ድጋፋችን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል’’ በማለት ጨምረው ገልጸዋል።

የሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር መስራችና ዋና ስ/አስኪያጅ አቶ ሚኪያስ ለገሰ በበኩላቸው እንደተናገሩት አቢሲንያ ባንክ ድጋፍ ሲያደርግላቸው ይህ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ገልጸው፣ ባንኩ በቀጣይም ከጎናቸው እንዲሆንና ድጋፉ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የባንካችን የስራ ሃላፊዎች እና ሠራተኞች ለአረጋውያኑ የምሳ ግብዣ ያደረጉ ሲሆን የምሳ ግብዣው ወጪ የተሸፈነው የመካከለኛው አዲስ አበባ ዲስትሪክት ሠራተኞች ከደሞዛቸው ካዋጡት ገንዘብ እንደሆነ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button