7 የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን በመጠቀም ማከናወን የሚችሏቸው ነገሮች

7 የአቢሲንያ ቪዛ ካርድን በመጠቀም ማከናወን የሚችሏቸው ነገሮች

በየትኛውም ቦታ ገንዘብን የመሸከም አስፈላጊነት በማስቀረት፣ ግብይትን እና ክፍያን ቀላል በማድረግ፣ ባንካችን የደንበኞች የካርድ ክፍያ ስርአት ተጠቃሚነት ላይ  በቅልጥፍና እና በጥራት እየሰራበት ሲሆን፣ የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ የተለያዩ አገልግሎቶችን መጠቀም እንዲያስችል ሆኖ የቀረበ ነው፡፡

አቢሲንያ ቪዛ ካርድን ሊገለገሉ የሚችሉባቸው መንገዶች፡-

ካርዱን በየትኛውም የባንኩ ኤ.ት.ኤም. ማዕከላት እንዲሁም በሌሎች ባንኮች  ኤ.ቲ.ኤም ማሸን ላይ መጠቀም የሚቻል ሲሆን፣ ካርዶቹን በመጠቀም የምናገኛቸው አገልግሎቶች ፡-

1-ንክኪ የሌለው አገልግሎት፡-   ካርዱን በኤቲኤም ማሽኖች ውስጥ ማስገባት ሳያስፈልግ ግብይቱን ካርዱን ብቻ በማስጠጋት ገንዘብ ወጪ ማድረግ

2-ወደ ቴሌብር ገንዝብ መላክ፡- የአቢሲንያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች ካርዳችውን በመጠቀም ኤ.ቲ.ኤም ማሽን ላይ የቴሌብር ሒሳባቸው ላይ ገንዘብ ማስተላለፍ

3-ከሂሳብ  ወደ ወደ ሂሳብ ገንዘብ ማስተላለፍ፡-  ደንበኞች በቀላሉ ካርዳቸውን በመጠቀም ወደ ሌላ የአቢሲንያ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ  ማስተላለፍ

4-ቀሪ ሂሳብን ማየት ፡- ግብይት ወይም ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ በሒሳብዎ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን ማወቅ

5-የአቢሲንያ ቪዛ ካርድዎን በመጠቀም በቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ POS ላይ ገንዘብ ወጪ ማድረግ

6-በተለያዩ የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣  ሱፐርማርኬቶች፣ ሆቴሎች፣ የእንግዳ ማረፊያ፣ ሆስፒታሎች ….የግብይት እና አገልግሎት ክፍያን በቀላሉ ማከናወን  

7-በሀገር ውስጥ የኢኮሜርስ ድረ-ገጾች ላይ ግብይት ማድረግ

የክፍያ ስርአታችውን  በአቢሲንያ ያደረጉ የንግድ ተቋማት ዝርዝር ከታች የሚገኘውን ማስፈንጠሪ በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡-

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button