ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ ከባንካችን ዋናው መ/ቤት እና ከአስሩም ዲስትሪክቶች የስራ ሃላፊዎች በተውጣጡ ቡድኖች መካከል የሚከናወነው የእግር ኳስ ውድድር በከፍተኛ ድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ የባንካችን የኮርፖሬት የሰው ሃብት ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሰይፉ ቦጋለ በተገኙበትና ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ልደታ ክ/ከተማ በሚገኘው ብሪሞ ሜዳ በተጀመረው የእግር ኳስ ውድድር ላይ ከዋናው መ/ቤት ሁለት ከዲስትሪክት ደግሞ 10 በጠቅላላው 12 ቡድኖች እየተሳተፉ ይገኛል።
ውድድሩ ጥር 30፣ 2018 ዓ.ም በሚከናወን የዋንጫ ጨዋታ የሚጠናቀቅ ሲሆን አምና በተካሄደው ተመሳሳይ ውድድር የዋናው መ/ቤት አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል፡፡






Leave a Reply