አቢሲንያ ባንክ በባንኪንግ ኢንደስትሪው ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን ያማከለ ቨርቸዋል የባንክ ማዕከል ሥራ አስጀመረ

አቢሲንያ ባንክ በባንኪንግ ኢንደስትሪው ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን ያማከለ ቨርቸዋል የባንክ ማዕከል ሥራ አስጀመረ

ባንካችን የአምስት ዓመት የስትራቴጂ ዕቅዱን ሲነድፍ ለደንበኞች ምቾቱን የጠበቀና የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በማሰብ ለዲጂታል ቴክኖሎጂ (Digitalization) ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አያሌ አበረታች ተግባራትን አከናውኗል፡፡

በዚህም መሠረት፣ ባንካችን በስልታዊ ዕቅዱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ አቢሲንያ ኦንላይን፣ ኢ-ኮሜርስ ፔይመንት ጌትዌይን የመሳሰሉ የኦንላይን የባንክ አገልግሎቶችን በመጀመር፣ እንዲሁም የክፍያ ማለትም የኤ.ቲ.ኤምና የፖስ መሣሪያ በማኅበረሰባችን ዘንድ ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቢሲንያ ባንክ በባንኪንግ ኢንደስትሪው ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነውን የቨርቸዋል የባንክ አገልግሎት ማዕከል መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በይፋ ማስተዋወቁ ይታወቃል፡፡ይህ የቨርቸዋል የባንክ አገልግሎት ማዕከል በባንካችን የደንበኛ አማካሪዎች በመታገዝ የተሟላ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በአይ.ቲ.ኤም. (Interactive Teller Machine) የሚታገዝና ደንበኞች ምቾታቸው ተጠብቆ በቀን ለ24 ሰዓት በሳምንት ለ7 ቀናት አገልግሎት የሚያኙበት ነው፡፡

ደንበኞች በዚህ ደኅንነቱ በተጠበቀ የቨርቸዋል ማዕከል ከሚያገኟቸው አገልግሎቶች መካከል;-

  • ሒሳብ መክፈት፤
  • ገንዘብ ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ፤
  • ቼክ መመንዘርና ተቀማጭ ማድረግ፤
  • የሃገር ውስጥ ሓዋላ፤
  • ገንዘብ ማስተላለፍ እና
  • እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ካርድ ባንኪንግና ሞባይል መኒ ያሉ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላል፡፡

አቢሲንያ ባንክ ይህ አገልግሎት ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችቹን ያማከለ እንዲሆን ለማድረግ ከወለድ ነጻ የቨርቹዋል ባንክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ቤተል አካባቢ በመክፈት ከሰኔ 05 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለክቡራን የባንኩ ደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑን በደስታ እናበስራለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button