የባንካችን ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ አስተማሪና አዝናኝ ፕሮግራሞች አክብረዋል።
በዚህ ለግማሽ ቀን በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደው ዝግጅት ላይ የባንካችን ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ በቃሉ ዘለቀን ጨምሮ የዋናው መ/ቤት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣የዋናው መ/ቤትና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የባንኩ ሠራተኞች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ታማኝነት አቢሲንያ ባንክ ካስቀመጣቸው አብይ እሴቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን በመግለጽ “ታማኝነት የማንነታችን መገለጫ የተግባር ማሳያ ነው፡፡ ታማኝነት ሥራን በሐቀኝነት እንዲሁም በሚዛናዊነት ማከናወን እና ለምናከናውናቸውም ተግባራት ኃላፊነት ወስዶ መሥራት መቻል ነው ” በማለት አብራርተዋል፡፡ አቶ በቃሉ አክለውም ታማኝነት ባንካችን ከማንም ጋር የማይደራደርበት አብይ እሴቱ በመሆኑ፣ የባንካችን ሠራተኞች ሁሌም በተግባር ልንኖረው ይገባል በማለት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይም ከፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዓሉን አስመልክቶ በድምፅ ተዘጋጅቶ የተላከ ሰነድም የተደመጠ ሲሆን ውይይትም ተደርጎበታል፡፡በተጨማሪም የባንኩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም የሃብት ምዝገባ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን በመጨረሻም ባለሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡
በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሃገራችን የሚከበረው የፀረ ሙስና ቀን ዘንድሮም ለ22ኛ ጊዜ “ትውልድን በስነ ምግባር ፣ ተቋምን በአሰራር !” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡










Leave a Reply