ባንካችን አቢሲንያ አብደላ ነዲም (ANM) ከኢንተርናሽናል ቴንስ ፌዴሬሽን (ITF) ጋር  በመተባበር ያዘጋጀውን ከ18 ዓመት በታች የሜዳ ቴንስ ውድድር ስፖንሰር አደረገ።

ባንካችን አቢሲንያ አብደላ ነዲም (ANM) ከኢንተርናሽናል ቴንስ ፌዴሬሽን (ITF) ጋር  በመተባበር ያዘጋጀውን ከ18 ዓመት በታች የሜዳ ቴንስ ውድድር ስፖንሰር አደረገ።

ከ32 ሀገራት የተውጣጡ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ተወዳዳሪዎች በኢቨንት ኦርጋናይዘር አብደላ ነዲም መሀመድ (ANM) ከኢንተርናሽናል ቴንስ ፌዴሬሽን (ITF) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ቴንስ ፌደሬሽን ግቢ ውስጥ ያዘጋጀው የሜዳ ቴንስ ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል። ውድድሩ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ታዳጊዎች አለም አቀፍ የተወዳዳሪነት ደረጃቸውን (World Rank) ለማሳደግ የሚሳተፉበት ሲሆን፣ ይህንን ውድድር ባንካችን አቢሲንያ “Abyssinia Open” በሚል ስያሜ ውድድሩን ስፖንሰር አድርጓል። 

በውድድሩ ላይ የባንካችን አርማ በድምቀት ከመታየቱ በተጨማሪ አሸናፊዎቹ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው አቀባበል በሚደረግላቸው ሰዓት  የባንካችን አርማ በፕሮግራሙ ላይ የሚሰቀል በመሆኑ ባንካችን በአለም አደባባይ የማስተዋወቅ ዕድል ያገኛል፡፡

ዝግጅቱን ምክንያት በማድረግ ከተወዳዳሪዎቹ በተጨማሪ የተወዳዳሪዎች አሰልጣኝ፣ ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ዕድሉን ያላገኙ የውጪ ዜጎች በዚህ ውድድር አጋጣሚ ሀገራችንን ማየት በመቻላቸው ውድድሩ የስፖርት ቱሪዝሙን ከማሳደጉ በተጨማሪ ጥቂትም ቢሆን አሁን ሀገራችን ለገጠማት የውጪ ምንዛሬ እጥረት ራሱን የቻለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ይህ ውድድር በ2 ዙር የሚካሄድ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ውድድር የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በወንዶች በኦስትሪያዊ ተወዳዳሪ Thilo Behrmann አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ሁለተኛው ዙር የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀመር ይሆናል።

ባንካችን አቢሲንያ ስፖርት ለጤና፤ ለሰላም፣ ለፍቅርና አብሮነት እንዲሁም ለወዳጅነት ያለውን ሚና በመደገፍ ብሎም የሀገራችንን የስፖርት ዘርፍ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ከዚህ በፊት የ2020 በቶኪዮ የተካሄደውን የፓራለምፒክ ውድድርን ጨምሮ በተለያዩ ጊዚያት የተከናወኑ ስፖርታዊ ውድድሮችን ሲደግፍ የቆየ ሲሆን ወደፊትም ከስፖርት ቱሪዝሙ ጎን በመቆም የበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያደርግ ይሆናል።  

በዚህ አጋጣሚ የ ሁለተኛው ዙር ውድድር በመካሄድ ላይ ስለሚገኝ በኢንተርናሽናል ቴኒስ ፌዴሬሽን ጊቢ ውስጥ በመገኘት ውድድሩን መመልከት ይቻላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button