“ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ይጀምሩ – ያድሱ እና ይደጉ” የተሰኘው የሽልማት መርሃ-ግብር መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ላይ የሃዩንዳይ አክሰንት ሴዳን ዘመናዊ መኪና ተሸላሚ ይፋ ሆኗል።
በዚህ የባንካችን ቺፍ ከስተመር ማኔጅመንት ኦፊሰር የሆኑት አቶ ደሳለኝ ይዘንጋው እና ሌሎች የባንካችን የበላይ የሥራ አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ሃዩንዳይ መኪና የሚያስገኘው የዕጣ ቁጥር 0006800691690 ሆኖ ወጥቷል።
በወጣው ዕጣ መሠረትም የባንካችን የፍልውሃ ቅርንጫፍ ደንበኛና በከተማችን በአንድ የግል የህክምና ክሊኒክ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ዮሴፍ ገ/መድህን የሃዩንዳይ አክሰንት ሴዳን ዘመናዊ መኪና ዕድለኛ ሆነዋል።
ከዚህም በተጨማሪ 3 ላፕቶፖችን፣ 3 ኤል.ኢ.ዲ ቴሌቪዥኖች እና አንድ የልብስ ማጠቢያ ማሽን በድምሩ 8 ዕጣዎች ለዕድለኞች ወጥተዋል።.
በዚህ መርሃ ግብር በአጠቃላይ 22 ሽልማቶች የተካተቱ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ይፋ ከተደረጉት 8 ሽልማቶች በተጨማሪ 14 ሽልማቶች ካሁን ቀደም ወጥተው ለዕድለኞች ተከፈፍለዋል። በመርሃ ግብሩ የባንካችንን የተለያዩ አገልግሎቶች ለተጠቀሙ ደንበኞች የተላኩ ከ11,500,000 በላይ የዕድል ቁጥሮች ተካተዋል።
ይህ መርሃ ግብር ባንካችን ከዚህ ቀደም ሲያከናውናቸው ከነበሩ የሽልማት መርሃ ግብሮች በአይነቱም ሆነ ዕጣዎቹ በየ15 ቀኑ በ3 ዙር የወጡበት ሁኔታ ልዩ የሚያደርገው ሲሆን፣ በቅርቡም በሌሎች አዳዲስ መርሃ ግብሮች ደንበኞቻችንን ለመሸለም ከምንጊዜውም የበለጠ ተዘጋጅቷል









Leave a Reply