አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
- የጨረታ ቦታ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሽረንደስላሴ ከተማ፣ ቀበሌ 04፣ አደባባይ ኃየሎም በሚገኘው የባንኩ ሽረንደስላሴ ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-515-11-53 እና 011-515-07-11 አ.አ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Leave a Reply